ኮለኔል ርጃል ኡመር የ108 ዓመት ወጣት እየተባሉ ነዉ፡፡
ኮለኔል ርጃል ኡመር የ108 ዓመት ወጣት እየተባሉ ነዉ፡፡
እንዴት ተደርጎ ካላችሁ ነገሩ እንዲህ ነዉ፡፡
ኮለኔል ርጃል ኡመር ይባላሉ፡፡ የ108 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ናቸዉ፡፡፡፡
እድሜያቸዉ 108 ይሁን እንጂ አሁንም የወጣትነት መልክ ነዉ የያዙት
የ108 ዓመቱ ኮለኔል ርጃል በ1903 ዓ.ም እንደተወለዱም ነው የሚናገሩት፡፡
ይሁን እንጂ እድሜቸው 108 መሆኑን ሲናገሩ ብዙዎቹ እንደማያምኗቸው ይናገራሉ
ለዚህም ጡረታቸውን ለማስከበር ወደ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባቀኑበት ወቅት አጭበርብረሃል በሚል ለአንድ ሳምንት መታሰራቸውን ያስታውሳሉ።
ከጥሬ ስጋ በስተቀር የበሰለ ስጋ እንደመይመገቡ የሚናገሩት ኮለኔሉ ስፖርትን የሚያዘወትሩና የሲጋራም ሆነ ሌሎች ደባል ሱሶች እንደሌሉባቸው ነው የገለጹት፡፡
ከአጼ ኃይለስላሴ ስርዓተ መንግስት ጀምሮ በውትድርና ያገለገሉ ሲሆን÷ በኮርያና በሩዋንዳ ለተለያዩ ወታደራዊ ተልኮዕዎችዎች ተልከው የነበረ መሆኑንም ይናገራሉ።
የመጀመርያ ልጃቸው በ85 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት እንደተለዩ የሚናገሩት ኮለኔል ርጃል ከ12 ትላልቅ ልጆቻቸው በስተቀር ትናንሾቹን በቁጥር እንደማያውቋቸው ነው የገለጹት።
አባታቸውም በ130 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሚናገሩት ኮለኔል ርጃል፥ ከዚህ በኋላም በሰውነታቸው አቋም ላይ የቅርፅ ለውጥ ሳይከሰት ለ10 ዓመት የመቆየት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ምንጭ ፤-ፋና