ሚኒስትር ዴኤታዋ የባህረ ሃሳብ መጽሃፍት እና ፍቅርና መቻቻልን የሚያስተምሩ መጽሐፍትን ለቀድሞ ትምህርት ቤታቸዉ ሰጡ ።
ሚኒስትር ዴኤታዋ የባህረ ሃሳብ መጽሃፍት እና ፍቅርና መቻቻልን የሚያስተምሩ መጽሐፍትን ለቀድሞ ትምህርት ቤታቸዉ ሰጡ ።
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ በተማሩበት የቅድስት ስላሴ ካቴድራል ትምህርት ቤት ተገኝተው ነዉ መጽሃፍት ያበረከቱትና ለተማሪዎችም የማነቃቂያ ንግግር ያደረጉት።
ወ/ሮ ሂሩት ለተማሪዎቹ ባደረጉት ንግግር ፤ የስኬት መሰረት ከመምህራንና ከቤተሰብ ከሚገኘው እውቀት በተጨማሪ በማንበብ፣ ጥረት በማድረግና በእችላላሁ መንፈስ በመስራት ነው ብለዋል።
ተማሪ አድጎ ቤተሰቡንና አገሩን መጥቀም የሚችለው ዛሬ ላይ በእውቀትና በስነ ምግባር ታንጾ ሲያድግና ዓላማቸው ጥሩ ከሆኑ ሰዎች ጋር በመተጋገዝ ዕውቀትና ልምድ ሲያዳብር እንደሁነም ወ/ሮ ሂሩት ተናግረዋል።
”ዛሬ ላይ መድረክ ላይ ወጥቼ ያለፍርሃት እንድናገር የቻልኩት በትምህርት ቤት ባዳበርኩት የስነጽሁፍ ውድድር፣ የቲያትር ትምህርት፣ የክርክርና የቤተሰብና የመምህራን ድጋፍ ነው”
መምህራን በቀጣይ አገርን ማገልገል ብዙ ዜጋን ለማፍራትና አንባቢ ትውልድን ለመፍጠር የግብረ-ገብና የሞራል ትምህርት በአግባቡ ማጠናከር እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ተማሪዎችም ከቤተሰብና ከመምህራንና ከሚያገኙት እውቀት በተጨማሪ በማንበብ፣ ጓደኛን በመውደድ፣ ከተንኮልና ከረብሻ በመራቅ የነገዋን ኢትዮጵያ እንዲረከቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ የዓለምን የስልጣኔ ምንጭ የሚዳስሱ፣ በኢትዮጵያውያን የተጻፉ የባህረ ሃሳብ መጽሃፍት እንዲሁም ፍቅርና መቻቻልን የሚያስተምሩ መጽሐፍትን ለትምህርት ቤቱ አበርክተዋል።