loading
415 ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ከፑንትላንድ ይመለሳሉ ፡፡

415 ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ከፑንትላንድ ይመለሳሉ ፡፡

በህገ ወጥ ደላሎች በመታለል በፑንትላንድ አድርገው በቦሳሶ በኩል ባህር አቋርጠው ወደ የመንና ሳኡዲ አረብያ ለመግባት ሲጓዙ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ከፑንትላድ አስተዳደር ጋር በመተባበር በራሳቸው ፈቃድ ወደ አገር ቤት የመመለስ ስራ በስፋት እየተሰራ ነው።

ህገ ወጥ ደላሎች ቦሳሶ ካደረሷቸው በኋላ በመንገድ ላይ በትነዋቸው እንደሚሄዱ የሚገልጹት ዜጎቻችን ፑንትላንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ከፑንትላንድ የክልል መስተዳደር ጋር በመተባበር ከእስር ቤት በማስወጣት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ይገኛል።

በእስካሁኑ አንቅስቃሴም 1000 ዜጎቻችንን ከፑንትላንድ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በማድረስ ወደየ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

በህገ ወጥ ደላሎች ከሚደርስባችው እንግልት ማምለጥ በመቻላቸው ደስተኞች መሆናቸውንም አኒነዚሁ ዜጎቻችን ገልጸዋል።

በዛሬው እለት ደግሞ  ኢትዮጵያዊያን ፑንትላንድ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በድንበር በኩል ወደ አገራቸው ይመለሳሉ።

በተመሳሳይ ከዓለም አቀፉ የስደተኞቸ ድርጅት ጋር በመተባበር 517 ዜጎቻችንን ለመመለስ አስፈላጊው የጉዞ ሰነድ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ነው፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *