የዓድዋ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማዋ ጸጥታ ምክር ቤት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ
የዓድዋ ድል በዓል በደማቅና ሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ገለጸ፡፡
የፀጥታ ምክርቤቱ የዓድዋ ፌስቲቫል እና የዓድዋ ድል በዓል አከባበርን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከተወያየ በኋላ መግለጫ አውጥቷል።
በዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል ከ500 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ያለው መግለጫው ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር እና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ዝግጅት በሙሉ ማጠናቀቁንም አስታውቋል፡፡
ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አንደሚያመለክተው በዕለቱ በዓሉን ለሚያከብሩ የከተማዋ ነዋሪዎች የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት በነፃ አገልግሎት ይሰጣል።