loading
በቻምፒዮንስ ሊግ ሊቨርፑልና ባርሴሎና ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል

በቻምፒዮንስ ሊግ ሊቨርፑልና ባርሴሎና ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል
ትናንት ምሽት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 16ቱ ቡድኖች የጥሎ ማለፍ ዙር የመጨረሻ ሁለት መልስ ግጥሚያዎች ተካሂደዋል፡፡
በምሽቱ በጉጉት በተሻለ በተጠበቀው የባየርን ሙኒክ እና ሊቨርፑል የአሊያንዝ አሬና ላይ ጨዋታ በቀያዮቹ የበላይነት ተደምድሟል፡፡
የዙሩ ተቀዳሚ ግጥሚያ አንፊልድ ላይ ያለግብ ቢጠናቀቅም፤ በምሽቱ የመልስ ጨዋታ በሊቬ 3 ለ 1 ድል አድራጊነት ተጠናቅቋል፡፡ ሴኔጋዊው ሳዲዮ ማኔ ሁለቱን እንዲሁም ተከላካዩ ቨርጅል ቫን ዳይክ አንዷን አስቆጥረው ክለባቸውን ወደ ሩብ ፍፃሜው አሻግረዋል፡፡ የሊቨርፑሉ ተከላካይ ጆል ማቲፕ የሙኒክን ማስተዛዘኛ ግብ አስገኝቷል፡፡
ቀያዮቹ አሸናፊ መሆናቸውን ተከትሎ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ አራተኛው የእንግሊዝ ቡድን ያደርጋዋል፡፡ የባየር ሙኒክ ስንብት ደግሞ አንድም የጀርመን ቡድን ቀጣዩን ዙር ሳይዋሀድ እንዲቀር አድርጎታል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ካምፕ ኑ ላይ ባርሴሎና ከ ሊዮን ተገናኝተው፤ የካታላኑ ቡድን አሸንፎ በዘንድሮው ውድድር ስፔንን የወከለ ብቸኛው ክለብ አድርጎታል፡፡
የመጀመሪያው ጨዋታ 0 ለ 0 ቢጠናቀቅም ባርሳ ሜዳው ላይ ያደረገውን የመልስ ግጥሚያ በ5 ለ 1 አሸናፊነት ተወጥቷል፡፡


አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ሁለት ግቦችን ሲያበረክት፤ ሁለት ግብ የሆኑ ኳሶቹን ለኦስማን ዴምቤሌ እና ዤራርድ ፒኬ አመቻችቶ አቀብሏል፤ ፊሊፕ ኮቲንሆ ሌላኛዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡ ሉካስ ቶዛርት የሊዮንን ከባዶ መሸነፍ ያዳነች ግብ ከመረብ አገናኝቷል፡፡
ትናንት ምሽት ሜሲ ሁለት ግቦችን ማስቆጠሩ በውድድር ዓመቱ ያስ ቆጠራቸውን የመድረኩን ጎሎች መጠን ስምንት ያረሰ ሲሆን ከሮበርት ሉዋንዶውስኪ ጋር እኩል ሆነዋል፤ በቻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ ደግሞ በአጠቃላይ 112ኛ ጎሉን ሲያስቆጥር፤ ካምፕኑ ኑ ባደረጋቸው 61 የቻምፒዮንስ ሊጉ ጨዋታዎች 62ኛ ጉሉን አስመዝግቧል፡፡
ባርሴሎና ወደ ተከታዩ ዙር መዋሀዱን ተከትሎ፤ ለ12 ተከታታይ የውድድር ዓመታት ሩብ ፍፃሜው ላይ በመድረስ ክብረወሰን ይዟል፡፡
ሩብ ፍፃሜውን ከተዋሀዱ ቡድኖች ውስጥ 50 በመቶው የእንግሊዝ ቡድኖች ሲሆኑ ሊቨርፑል፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ቶተንሃም እና ማንችስተር ዩናይትድ ናቸው፤ ከስፔን ባርሴሎና፣ ከጣሊያን ዩቬንቱስ፣ ከፖርቱጋል ፖርቶ እንዲሁም ከኔዘርላንድስ አያክስ ዙሩን መቀላቀላቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው፡፡
በመጭው አርብ የሩብ ፍፃሜው የዕጣ ማውጣት ሰነ ስርዓት ይከናወናል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *