loading
የዓለም ህዝብ ቁጥር በፈረንጆቹ 2050 9.7 ቢሊዮን ሊደርስ ይችላል ተባለ፡፡

የዓለም ህዝብ ቁጥር በፈረንጆቹ 2050 9.7 ቢሊዮን ሊደርስ ይችላል ተባለ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በስነ ህዝብ እና ልማት ላይ ባተኮረ ስብሰባው ይፋ ባደረገው ሪፖርት ነው ይህን ያለው ፡፡

ሲጂቲኤን እንደዘገበው አሁን ያለው የዓከም ህዝብ ቁጥር ወደ 7.7 ቢሊዮን እንደሆነ የሚገመት ሲሆን ከ2050 በኋላም ሩቅ በማይባል ጊዜ እስከ 11 ቢሊዮን ሊደርስ እንደሚችል የጥናቱ ትንበያ ያሳያል፡፡

የዓለማችን ህዝብ እንዲህ በፍጥነት ማሻቀቡ በተፈጥሮ ሀብት እና በአካባቢ ስነ ምህዳር ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚያሳድር ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የህዝብ ቁጥርን ከሚያባብሱት ምክንያቶች መካከል አንዱ የከተሞች መስፋፋት መሆኑን የድርጂቱ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናግረዋል፡፡

ይህም የሚሆነው ከተሜነት በተስፋፋ ቁጥር የጤና አጠባበቅ ልምድ ስለሚቀየር፣ ሞት ስለሚቀንስ እና የሰዎች አማካይ የመኖር እድሜ ከፍ ስለሚል ነው ተብሏል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *