ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ነቀምቴ ከተማ ገቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ነቀምቴ ከተማ ገቡ
በነቀምቴ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም የወለጋ ስታዲየምን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መርቀው እንደሚከፍቱ ይጠበቃል ብሏል ፋና በዘገባዉ።
በዛሬው እለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚደረገው በነቀምቴ ከተማ የሚገኘው የወለጋ ስታዲየም ግንባታ በመንግስት እና በህብረተሰቡ ድጋፍ የተከናወነ ነው።
ለግንባታው እስካሁን 196 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፥ ከዚህም ውስጥ 181 ነጥብ 7 ሚሊየን ብሩ በመንግስት የተሸፈነ መሆኑ ተነግሯል።
ከ30 ሺህ በላይ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ስታዲየሙ፥ በዙሪያው ለቢሮና ለንግድ የሚያገለግሉ ሱቆችም አሉት።
ስታዲየሙ በፊፋ መመዘኛ መሰረት ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እየተሰራ ሲሆን፥ የእግር ኳስ፣ የቦሊቦልና የቅርጫት ኳስ ሜዳዎች፣ የመሮጫ መምና ሌሎች የመወዳደሪያ ሥፍራዎችን ያካተተ ነው።