ፌዴራል ፖሊስ በሙስናና በኢኮኖሚ አሻጥር ወንጀሎች የጠረጠራቸውን 61 የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አዋለ
ፌዴራል ፖሊስ በሙስናና በኢኮኖሚ አሻጥር ወንጀሎች የጠረጠራቸውን 61 የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አዋለ።
ከታሳሪዎቹ መካከል የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባ ይገኙበታል ተብሏል።
አዲስ ፎርቹን ድረገጽ እንደዘገበው ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋለው ከትናንት ማለዳ ጀምሮ ባካሄደው ዘመቻ ነው።
በቁጥጥር ሰር ከዋሉት ባለስልጣናት ውስጥ የቀደመው የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ የግዢና ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ አገልግሎት፣ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍና አቅርቦት ኤጀንሲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የስራ ሃላፊዎች ይገኙበታል ተብሏል።
የጠቅላይ ዐቃቢህግ ቢሮ ይህንን አስመልክቶ ዛሬ ማምሻውን መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።