ኢትዮጵያ የቡድን 77 እና ቻይና ሊመንበርነቷን በስኬት ማጠናቀቋ ተገለጸ
ለአንድ ዓመት የዘለቀውን የቡድን 77 እና ቻይና የናይሮቢ ቻፕተር ሊቀመንበርነቷን በስኬት ማጠናቀቋን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ ለዚህ ተቋም ስኬት ጠንክራ እንደምትሰራ ቃል ገብታለች።
የቡድን 77 እና ቻይና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 134 የአፍሪካ፣ ኤዥያ እና ላቲን አሜሪካ አገራትን ያጠቃለለ ጠንካራው ስብሰባው ነው። ቡድኑ በዓለም አቀፍ መድረኮች ለታዳጊ አገሮች ጥቅም ጠበቃ በመሆን ይታወቃል ይላል የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት መግለጫ።
በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር መለስ ዓለም የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆነው የፍልስጤም አስተዳደደር ሊቀመንበርነቱን ካስረከቡ በኋላ ባደረጉት ንግግር ህብረቱ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ጠበቃ እንደሆነ ጠቅሰው ለስብስቡ መጠናከር ኢትዮጵያ አበክራ ትሰራለች ብለዋል።
በኬንያ የተ.መ.ድ ዋና መ/ቤት የፍልስጤም አስተዳደር ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሃዚም ሻባት ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነቷ ላደረገችው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልፀዋል ተብሏል።