loading
በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮዽያውያ እና ትውልደ ኢትዮዽያውያን የተሳተፉበት ውይይት ተካሄደ

በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮዽያውያ እና ትውልደ ኢትዮዽያውያን የተሳተፉበት ውይይት ተካሄደ

የኢትዮዽያ ኤምባሲ በስውዲን ከሚገኙ ኮሚኒቲዎች ጋር በመተባበር በአገሪቱ ከሚኖሩ ኢትዮዽያውያን እና ትውልደ ኢትዮዽያውያን የተሳተፉበት ውይይት በስቶክሆልም ከተማ አካሂዷል፡፡

በስዊድንና በሌሎች የኖርዲክ አገራት አምባሳደር ድሪባ ኩማ በአገራችን አጠቃላይ የለውጥ ሥራዎች ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ባለፈው አንድ አመት በፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ዘርፎች በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱ፣ በውጭ አገራት የነበሩ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ አገራቸው ገብተው በሰላማዊ መንገድ እንዲሳተፉ መደረጉንና ሎሎችን ለአብነት አንስተዋል።

የጸረ ሽብር አዋጅ፣የበጎ አድራጎት አና ማህበራት አዋጅ እና የመረጃ ነጻነትና የሚዲያ አዋጅ እንዲሻሻሉ በማድረግ የዴሞክራሲ ምህዳሩ እንዲሰፋም ተግባራዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋለ።

በአገራችን የሚካሄደዉ ቀጣዩ ምርጫ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና በመራጮች ዘንድ ተቀባይነት ያለዉ እንዲሆን ለማድረግ የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያ እና የተቋም አቅም ግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል።

በኢኮኖሚዉ ዉስጥ የግል ዘርፉን ሚና ለማጠናከር ፣የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የአገራችንን ኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት እንዲኖረዉ ለማድረግ ፣ለዜጎቻችን የስራ ዕድል የሚፈጠርበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በርካታ የህግ ማዕቀፍና የአሰራር ማሻሻያ ጥናቶች እየተካሄዱና በተግባር ላይ እየዋሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *