loading
የፌደራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አላግባብ የተያዙ ማምረቻ ቦታዎችን ማስመለስ አለበት ተባለ፡፡

የፌደራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በስራ ፈጠራ፣  የዋሉ ብድሮችንና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በላይ የቆዩ የማምረቻና መሸጫ ሼዶችን በማስመለስ ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ተገለፀ፡፡
ይህ የተጠቆመው የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኤጀንሲው ባደረገው የመስክ ምልከታ ወቅት ነው፡፡
ቋሚ ኮሚቴዉ  የኤጀንሲውን የስራ እንቅስቃሴ ቃኝቷል፤ በቁልፍ ተግባራት አፈጻፀምና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያም የኤጀንሲውን የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኞችን አወያይቷል፡፡
በውይይቱም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ኩሞ በስራ ዕድል ፈጠራ በኩል በ6 ወራት ውስጥ ያለው አፈጻጸም 80% መድረሱን በከተማ የምግብ ዋስትና በ11 ከተሞች ከ445 ሺህ በላይ ዜጎች በዘላቂ ድጋፍና በሴፍቲኔት ፕሮግራም በአካባቢ ልማት ላይ በመሳተፍ ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
አመላመላቸውም በህብረተሰቡ በቂ ግምገማ ተደረጎ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የአለም ባንክ ሂደቱን በጥሩ አፈጻጸም የገመገመ በመሆኑ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ሀላፊው የተናገሩት፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የመስሪያ ቦታ፣ ብድር እና ሼዶችን በማስመለስ ሂደት ላይ የሚስተዋሉትን ችግሮች በእጥረት አንስተዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ እየታየ ያለው መቀዛቀዝ እና የማምረቻና የመሸጫ ሼዶችን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለምን ማስመለስ እንዳልተቻለ የጠየቁ ሲሆን፤ የስራ እድል ፈጠራው የተቀዛቀዘው በአገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት መሆኑን፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚዎች የሚሰጡ የማምረቻና የመሸጫ ሼዶች ለ5 አመታት ቢሆንም 10 እና ከዚያም በላይ አመታት ተጠቅመው ያልመለሱ አካላት መኖራቸው ተጠቁሞ በቀጣይ እነዚህን አካላት በመለየት የማስመለስ ስራ እንደሚሰራ ነው የኤጀንሲው የስራ ሃላፊዎቹ ምላሽ የሰጡት፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት የኤጀንሲውን የለውጥና የመልካም አስተዳደር፣ የሴቶችጉዳይ፣ የውስጥ ኦዲት፣ የሂሳብና የንብረት አስተዳደር ክፍሎችን የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው ተመልክተዋል፡፡
የኤጀንውን ሰራተኞች ባወያዩበት ወቅትም በአገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች ያለው አለመረጋጋት ስራቸውን ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ለመስራት ስጋት እንዳሳደረባቸው፣ የሚከፈላቸው የቀን አበልም የወቅቱን የኑሮ ደረጃ ያላገናዘበና የቢሮ አጥረትም ጭምር እንዳለባቸው ሰራተኞች ለቋሚ ኮሚቴ አባላት ተናግረዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *