ዛሬ ምሽት በቶተንሃም እና አያክስ መካከል የቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ይደረጋል
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይከናወናሉ፡፡
የእንግሊዙ ቶተንሃም ሆተስፐር በአዲሱ ስታዲየም ዛሬ ምሽት 4፡00 ላይ የኔዘርላንድሱን አያክስ አምስተርዳም የሚገጥም ይሆናል፡፡
በአሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ እየተመሩ በቻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የግማሽ ፍፃሜ ተሳትፏቸውን እያደረጉ የሚገኙት ስፐርሶች ፤ በኢሪክ ቴን ሃግ ከሚመራው የበርካታ ወጣቶች ስብስብ እና ታላላቅ ቡድኖችን ጭምር ከውድድር እያሰናበተ እዚህ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ ደግሞ ባለተራው የእንግሊዙ ቡድን ይሆን የሚለው ይጠበቃል፡፡
ስፐርሶች የጎል አዳኛቸውን ሃሪ ኬን ግልጋሎት በጉዳት ምክንያት በምሽቱ የማያገኙ ሲሆን ቡድኑ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ቁልፍ ሚና የነበረው ደቡብ ኮሪያዊው ሶን ሂንግ ሚን በቅጣት ምክንያት በጨዋታው የማይኖር ይሆናል፡፡ አማካዩ ሙሳ ሲሶኮ ልምምድ ጀምሯል፡፡
በሆላንድ ኢርዲቪዚዬው ፒ.ኤስ.ቪን በግብ ክፍያ በመብለጥ ቀዳሚ ደረጃ ላይ የሚገኘው አያክስ ከ1996/97 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፍፃሜ ተፋላሚ ለመሆን እያለመ ወደ ለንደን ተጉዟል፡፡
ነገ ምሽት ሌላኛው ተጠባቂ ግጥሚያ በባርሴሎና እና ሊቨርፑል መካከል ኑ ካምፕ ላይ ይደረጋል፡፡