በኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የማሳድጋቸዉን ህጻናት እንዳልበትን ደግፉኝ አለ፡፡
አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 በኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕጻናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የማሳድጋቸዉን ህጻናት እንዳልበትን ደግፉኝ አለ፡፡
ድርጅቱ ለአርትስ ባላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ በ1965ዓ.ም በሃገራችን ከተከሰተዉ ድርቅ ጋር በተያያዘ ቤተክርስተያን በወቅቱ ተገቢዉን ምላሽ ለመስጠት 36 የህጻናት መርጃ በማቋቋም የተመሰረተ እንደነበር ገልጿል፡፡ከተመሰረተ ጀምሮም ባለፉት 45 ዓመታት አስካሁን ከ42 ሺህ በላይ ሕጻናትን እንዳሳደገ በመግለጫዉ ጠቅሷል፡፡ድርጅቱ አሁን ከዉጪ የሚያገኘዉ ዕርዳታ ከጊዜ ወደጊዜ በመቀነሱ ምክንያት፤18 የህጻናት መርጃ ማዕከላት ብቻ እንደቀሩና አሁንም በማዕከሉ ዉስጥ ድጋፍ እየተደረገላቸዉ የሚገኙ 39 ሺህ 150 ወላጅ አጥ ህጻናትና ችግረኛ ቤተሰቦችን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ድጋፍ እንዳይቋረጥ ችግር ዉስጥ እንዳይገቡ ስጋት ዉስጥ መሆኑን ገልጿል፡፡ከኮሮና ቫረስ ጋር በተያያዘም ድርጅቱ ድጋፍ እየሰበሰበ እንደሆነ እና የደረቅ ምግብ ፤የቁሳቁስ፤ መድሀኒት እና የሕክምና መሳርያዎችን በቀላሉ ለመቀበል እና ለሚስፈልጋቸዉ ለማድረስ አደዋ ድልድይ በሚገኘዉ ቢሮ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡
ባጠቃላይ ድርጅቱን ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ እና ከገባባት የኢኮኖሚ ችግር ለመዉጣት 6650 A የገቢ ማሰባሰቢያ ማዘጋጀቱን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡