የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በልብ ህመም በድገንገት ህይዎታቸው አለፈ ::
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በልብ ህመም በድገንገት ህይዎታቸው አለፈ ::የብሩንዲ መንግስት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንቱ በልብ ህመም መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ቅዳሜ በአንድ የቮሊቦል ጨዋታ ውድድር ላይ ታድመው የነበረ ሲሆን በዚያው ምሽት ታመው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ሰኞ እለት በተደረገላቸው ምርመራ የልብ ችግር እንደገጠማቸው እና ለሞት እንዳበቃቸው ነው የተነገረው፡፡ ንኩሪንዚዛ ብሩንዲን ለ15 ዓመታት ከመሩ በኋላ በዘንድሮው ምርጫ እንደማይሳተፉ ቀድመው በማሳወቅ የፓርቲያቸውን የቅርብ ሰው በእጩነት አቅርበው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ
መወሰናቸው ይታወሳል፡፡ የተለያዩ ሀገራት መሪዎ በ55 ዓመቱ ፒዬር ንኩሪንዚዛን ሞት ተከትሎ የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
በሀገሪቱ የሰባት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን እንደሚደረግ የብሩንዲ መንግስት በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡