loading
የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በወር 20 ሚሊዮን ዶላር ይከፈላቸው ነበር ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በወር 20 ሚሊዮን ዶላር ይከፈላቸው ነበር ተባለ:: የሀገሪቱ የፀረ ሙስና ኮሚቴ ሰነድ ሳገላብጥ አገኘሁት ብሎ ይፋ ባደረገው መረጃ አልበሽር ይህን ያክል መጠን ያለው ደሞዝ ይከፈላቸው የነበረው ካልታወቀ ምንጭ ነው፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አልበሽር ደቡብ ሰዳን ራሷን ችላ ሀገር እንስክትሆን ድረስ ወርሃዊ ደሞዛቸው 20 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር በምርመራ ተደርሶበታል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ወርሃዊ ክፍያ በአንድ ወቅት ወደ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ያለ ሲሆን አሁን ባለው የሉዓላዊ ምክር ቤት ሰዎች ከስልጣናቸው እስኪወርዱ ድረስ ይከፈላቸው የነበረው ዝቅተኛው ደሞዛቸው 3 ሚሊዮን ዶላር ነበር ተብሏል፡፡ አልበሽር ከስልጣናቸው በህዝባዊ አመፅ ከተወገዱ በኋላ ቤታቸው ሲበረበር በርካታ የውጭ ሀገር ገንዘቦች እንደተገኘባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህም ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተገናኘ ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል፡፡
በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚፈለጉት አልበሽር በሀገር ቤት በተወሰኑ ወንጀሎች ፍርድ ቢያገኙም ገና ያልተቋጩ ክሶች አሉባቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *