loading
የአፍሪካ ህብረት በደቡብ ሱዳን ላይ ግዴታሽን አልተወጣሽም በማለት ማዕቀብ ጣለባት::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 የአፍሪካ ህብረት በደቡብ ሱዳን ላይ ግዴታሽን አልተወጣሽም በማለት ማዕቀብ ጣለባት::በየኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ልዩ መልዕክተኛ በሰጡት ማረጋገጫ ሀገሪቱ የሚጠበቅባትን መዋጮ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መክፈል ባለመቻሏ ነው ማዕቀቡ የተጣለባት፡፡ሺንዋ የዜና ወኪል እንደዘገበው ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረት ያልከፈለችው ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ የመዋጮ እዳ አለባት ፡፡በዚህም መሰረት ግዴታዋን ተወጥታ ህብረቱ ውሳኔውን ካላነሳላት ደቡብ ጁባ በህብረቱ ስብሰባዎች መሳተፍ እና ድምጿን ማሰማት አትችልም፡፡ወጣቷ ሀገር እየተባለች የምትጠራውና ከአፍሪካ ሀገራት 54ኛ ሆና በአባልነት የተመዘገበችው ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቀጠናዊና አለም አቀፋዊ እዳዎችም አሉባት ነው የሚባለው፡፡
ለአብነት ያህልም ኢስት አፍሪካን ኮሚዩኒቲ ለተባለው ተቋም ያልከፈለችው 24 ሚሊዮን ዶላር መክፈል እንደሚጠበቅባት ተነግሯታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *