loading
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እኩልነት የሰፈነባትን ዓለም እንፍጠር ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ13፣ 2012 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እኩልነት የሰፈነባትን ዓለም እንፍጠር ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡ የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዓለም በኮቪድ 19 በተቸገረችበት በአሁኑ ወቅት ሁሉም ህዝቦች እኩል ድጋፍ እያገኙ አይደለም የሚል መልእክት ነው ያስተላለፉት፡፡ ጉቴሬዝ ይህን ያሉት 101ኛው የኔልሰን ማንዴላ የልደት መታሰቢያ ቀን ላይ ባደረጉት የቪዲዮ ንግግር ነው፡፡ የዓለማችን አሳዛኝ ክስተት የሆነው ኮሮናቫይረስ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ሲባል በተዘረጋ ድንበር የመዝጋት ፖሊሲ የንግድ እንቅስቃሴዎች በመዳከማቸው ትልቅ የሀብት ልዩነት ተፈጥሯል ነው የተባለው፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ድሀ ሀገሮች ጫናውን መቋቋም እንዲችሉ ፍትሃዊ የድጋፍ ስርጭት ሊኖር ይገባል ሲሉ ዋና ጸሀፊው አሳስበዋል፡፡ አንዳንድ ሀገራት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በድጋፍ ስም ቅድመ ሁኔታዎችን በማብዛት ቅኝ ግዛትን በእጅ አዙር የማካሄድ አዝማሚያ እያሳዩ እንደሆነም ጉቴሬዝ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *