loading
በሐረሪ ክልል ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች ተደራሽ የሚያደርግ የኮሮረና ቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ነሃሴ 1 እንደሚጀመር የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ ።

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012 በሐረሪ ክልል ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች ተደራሽ የሚያደርግ የኮሮረና ቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ነሃሴ 1 እንደሚጀመር የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ ። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የኮሮና መከላከል ግብረሃይል ጸሃፊ አቶ ፈቲህ መሀዲ በሰጡት መግለጫ በክልሉ በአሁኑ ወቅት ስርጭቱ እየጨመረ ያለው የኮሮና ቫይረስ ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተለይም ከነገ ጀምሮ ለሚከናወነው የተጠናከረ የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የኮሮና ቫይረስ ናሙና ምርመራ ዘመቻ ስኬታማነት ከሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ አስፈላጊ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።

ለሁለት ሳምንታት የሚካሔደው ዘመቻ ውጤታማ ለማድረግ ከወረዳ አመራሮችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር በቂ ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል ። በዘመቻው በየቀኑ በአማካይ 863 ሰዎች በአጠቃላይ ደግሞ 12 ሺህ 85 ሰዎችን ተደራሽ የሚያደርግ የኮሮና ቫይረስ ናሙና ምርመራ የሚካሔድ ሲሆን ጎን ለጎንም በመከላከያ መንገዶች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማሳደጊያ ትምህርትና ቅስቀሳ ስራ ይከናወናል ።

በተጨማሪም ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጡ ክልከላዎችንና አዋጆችን አፈፃፀም ላይ የነበሩ ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችሉ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላትና ህብረተሰቡ ለዘመቻው ስኬት ሚናቸውን በላቀ ደረጃ እንዲወጡ አቶ ፈቲህ ጥሪ አቅርበዋል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *