የፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለምርጫ በእጩነት መቅረብ ኮትዲቯራያዊያንን አስቆይቷል::
አዲስ አበባ፣ነሐሴ08፣ 2012የፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለምርጫ በእጩነት መቅረብ ኮትዲቯራያዊያንን አስቆይቷል:: ፕሬዚዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ የሀገሪቱ ህገ መንግስት ስለማይፈቅድላቸው ቦታውን ለሌሎች ይልቀቁ የሚል ጥያቄ ይዘው ነው ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት፡፡ ዛሬ ለተቃውሞ የወጣነው ህግ ሲጣስ እያየን ዝም አንልም ብለን ነው ያሉት ተቃዋሚዎቹ መላው የኮትዲቯር ህዝብ ተቃውሞውን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የቀድሞውን የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ሎረን ባግቦን ጨምሮ በርካታ ተቃዋሚዎች ኦታራ ስልጣናቸውንእንዲለቁ በይፋ ጠይቀዋል ነው የተባለው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን እንዲህ ያለውን ድጋፍ የሌለውን አሰራር ማስቆም ባለመቻሉ ገለልተኛነቱ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2011 ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር የተዘጋጁት ከሁለት ዓመት በላይ መወዳደር የማይፈቅደውን የሀገሪቱን ህገ መንግስት በ2016 በማሻሻል ነው፡፡ ከአስር ዓመታት በፊት በኮትዲቯር በተካሄደው ምርጫ ተፎካካሪዎቹ በውጤቱ ባለመስማማታቸው ምክንያት በተነሳው ብጥብጥ ከ3 ሺህ በላይ ዜጎች ህይዎታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡