loading
በአውሮፓ የኮሮናቫይረስ ስርጭት መጨመሩ እንዳሳሰበው የዓለም ጤና ድርጅት ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013  በአውሮፓ የኮሮናቫይረስ ስርጭት መጨመሩ እንዳሳሰበው የዓለም ጤና ድርጅት ገለፀ:: ድርጅቱ በሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው በአውሮፓ በሳምንት ውስጥ የበሽታው ስርጭት በማርች ወር ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር የበለጠ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ አህጉር ሪጂናልን ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሃንስ ክሉግ አሁን ላይ በአህጉሩ እየታየ ያለው የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ብለዋል፡፡

በአወሮፓ ባለፈው ሳምንት በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ብዛት ከ300 ሺህ በላይ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህ አሃዝ ባለፈው ማርች ወር በሽታው ተባባሰ ተብሎ በተነገረበት ወቅት 264 ሺህ ገደማ እንደነበር ተመልክቷል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ባለፉት ሁለት ሳምነታት ብቻ ከግማሽ በላይ በሚሆኑት የአውሮፓ ሀገራት
የቫይረሱ ስርጭት በአስር በመቶ ጨምሯል፡፡ የአውሮፓ ሀገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያደርጉት የጋራ ጥረት ተጠናክሮ ካልቀጠለ ችግሩ
ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አሁን ላይ በዓለማችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሚሊዮን በላይ ያሻቀበ ሲሆን የሟቾች
ቁጥር ደግሞ ከ950 ሺህ በላይ ደርሷል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *