loading
በሞዛምቢክ እየተባባሰ የመጣው የሽብር ጥቃት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት ዳርጓል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 በሞዛምቢክ እየተባባሰ የመጣው የሽብር ጥቃት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት ዳርጓል ተባለ:: በሀገሪቱ በምንግስት ወታደሮች እና ነፍጥ አንግበው ጥቃት በሚያደርሱ ታጣቂዎች መካከል የሚደረገው ውጊያ በርካታ ዜጎችን የእንግልትና የስቃይ ሰለባ አድርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ በተባለው አካባቢ ታጣቂዎቹ የሚያደርሱት ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በዚህም ሳቢያ ከ310 ሺህ በላይ የሚሆኑ የገሪቱ ዜጎች ህይዎታቸውን ለማትረፍ ሲሉ መኖሪያ ቀያቸውን ለቀው መሰደድን ሳይወዱ ምርጫቸው አድርገዋል፡፡የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባወጣው ሪፖርት ጥቃቱን በመሸሽ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ብሏል፡፡ በግጭቱ ምክንያት ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በሽዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ድንበር አቋርጠው ወደ ታንዛኒያ ለመሰደድ ተገደዋል፡፡

በሞዛምቢክ አክራሪ ጂሀዲስት ሚሊሻዎች እንደ አውሮፓዊያዊ አቆጣጠር ከ2017 ጀምሮ በሲቪል ነዋሪዎች ላይ በሚያደርሱት ጥቃት ያለመረጋጋት ችግር ተባብሶ መቀጠሉ ይነገራል፡፡ ችግሩን ለመፍታት የቀጠናው ሀገራት መሪዎች ተደጋጋሚ ውይቶችን ቢያካሂዱም እስካሁን ይሄ ነው የሚባል መፍትሄ ማምጣት አልቻሉም ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *