loading
በዞኑ 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች በህንጻ ግንባታ ተለወጡ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 በዞኑ 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች በህንጻ ግንባታ ተለወጡ::በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች ወደ ህንጻ ግንባታ መለወጣቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።በሰሜን ወሎም ከ56 ሚሊዮን ብር ባላይ ወጭ የተገነቡ ትምህርተ ቤቶች ለአገልግሎት መዘጋጀታቸው ተነግሯል ።

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ትምህርት መምሪያ የግንባታ መሃንዲስ አቶ አራጋው አዲሱ ለኢዜአ እንደገለጹት :በተጠናቀቀው በጀት አመት የመማሪያ ክፍሎቹን ወደ ግንባታ ለመለወጥ 86 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጓል::ለግንባታው ወጭ የተደረገው ገንዘብ በመንግስት፣ በሰቆጣ ቃልኪዳን ስምምነት ፣ በቢ አይ ካ ቢዝነስ ግሩፕ፣ በአትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴና በህዝቡ ተሳትፎ የተሸፈነ መሆኑን ተናግረዋል ።

ከክልሉ ትምህርት ቢሮና ከግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለመማሪያ ክፍሎቹ የተማሪዎች መቀመጫና ሌሎች ቁሳቁሶች ለማሟላት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል ።በመምሪያው የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተጠሪ አቶ ፋንታው ስዩም በበኩላቸው በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከ882 በላይ የዳስ ጥላ መማሪያ ክፍሎች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የሰቆጣ ቃልኪዳን ስምምነት የዳስ መማሪያ ክፈሎቹን ወደ ግንባታ ለመለወጥ 42 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል ።በተያዘው በጀት አመትም 44 የዳስ መማሪያ ክፍሎችን ወደ ግንባታ ለመቀየር ማቀዱን አስታውቀዋል።በተመሳሳይ በሰሜን ወሎ ዞን በ58 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ወጪ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 50 ትምህርት ቤቶች ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታውቋል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *