loading
በማሊ የወባ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ በርካቶችን ለሞት መዳረጉ ተነገረ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 በማሊ የወባ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ በርካቶችን ለሞት መዳረጉ ተነገረ::በሰሜናዊ ማሊ ግዛት የወባ ወረርሽኝ መቀስቀሱንና በአንድ ሳምንት ውስጥ 23 ሰዎች መሞታቸውን የጤና ባለሙያዎች ይፋ አድርገዋል

የማሊ ጤና ሚኒስቴር በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል 59 ሰዎች በወረርሽኙ ምክኒያት መሞታቸውን አስታውቋልይህም የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር በእጥፍ ማደጉ ነው የተገለፀው

ከኮሮናቫይረስ ጋር ብርቱ ትግል የተያያዘችው ደሃዋ የሳህል ቀጣና ሀገር በማዕከላዊና ሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ከሚንቀሳቀሱ አክራሪ ጂሃዲስቶች ጋር የምታደርገው ግብግብ ሌላው እራስምታት ሆኖባታል ነው የተባለው::

የጤና ባለሙያዎች በሰሜናዊ ማሊ በፈረንጆቹ ከሴፕቴምበር 21 እስከ 27 ድረስ ባለው ጊዜ 13 ሺህ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን ተናግረው ካለፈው ሳምንት የ88 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል::በእነዚህ ቀናት ብቻ 23 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ጠቅሶ አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *