loading
ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ምርጫውን የማሸነፍ እድላቸው ሰፊ ነው እየተባለ ነው::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ምርጫውን የማሸነፍ እድላቸው ሰፊ ነው እየተባለ ነው::የኮትዲቯሩ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ የድምፅ ቆየጠራው ባይጠናቀቅም ከወዲሁ በሰፊ ልዩነት እየመሩ መሆናቸው እየተወራ ነው፡፡ ይህን የሰሙ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች ደጋፊዎቻቸውን ለተቃውሞ እዲዘጋጁ ጥሪ አስተላልፈዋል ነው የተባለው፡፡

የተቃዋሚ ፓር ወክለው የተወዳሩት ሄንሪ ቤዲ እና ፓስካል አፊ ንጉዌሳን በጋራ በሰጡ መግለጫ በምርጫው ምክንያት 30 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ ስለ ሟቾቹ ማንነትና ስለግድያቸው ሁኔታ ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ እንዳልሰጡ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ የኦታራን የማሸነፍ ቅድመ ግምት ያልተቀበሉት ተቃዋሚዎቹ የሽግግር መንግስት እዲቋቋም ጥሪ ማቅረባቸውም ተሰምቷል ነው የተባለው፡፡

ለሶስተኛ ጊዜ የተወዳደሩት ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ለምርጫ እጩ ሆነው መቅረባቸው ህገ መንግስታዊ አይደለም የሚል ክርክር በማስነሳቱ ግጭት ተቀስቅሶ በርካታ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2010 ፕሬዚዳንት ሎረን ባግቦና የአሁኑ ፕሬዚዳንት ኦታራ ባደረጉት የምርጫ ፉክክር በተፈጠረ አለመግባባት በመላ ሀገሪቱ ብጥብጥ ተነስቶ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *