በኢኳቶሪያል ጊኒ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ በደረሰ ፍንዳታ 20 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡
አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 በኢኳቶሪያል ጊኒ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ በደረሰ ፍንዳታ 20 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ በወታደራዊ ካምፑ ላይ አራት ከፍተኛ ፍንዳታዎች መድረሳቸው የታወቀ ሲሆን ከሞቱት 20 ሰዎች በተጨማሪ 600 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡
ፍንዳታው የደረሰው የኢኮኖሚ ከተማ በሆነችው ባታ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ንኮማ ንቶማ ወታደራዊ ካምፕ ነው፡፡
የፍንዳታው መንስኤ በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች በማሳቸው ላይ የሚገኙ የሰብል ቅሪቶችን ሲያቃጥሉ የተስፋፋ የእሳት ቃጠሎ ነው ተብሏል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንዘገበው የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር በፍንዳታው ምክንያት የሞቱና የቆሰሉትን ሰዎች ቁጥር ትክክለኛነት ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡
የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቴውዶሮ ኦቢያንግ በመግለጫቸው የካፕምፑ ሀላፊዎች በፈጠሩት ቸልተኝነት አደጋው መከሰቱን ገልፀዋል፡፡
ምክንያቱም በካምፑ ውስጥ የተከማቹ ተቀጣጣይ መሳሪያዎች በጥንቃቄ መቀመጥ ነበረባቸው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡