በናይጄሪያ 30 ወታደሮች በእስላማዊ ታጣቂ ሀይሎች መገደላቸዉ ተሰማ::
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 በናይጄሪያ 30 ወታደሮች በእስላማዊ ታጣቂ ሀይሎች መገደላቸዉ ተሰማ:: በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ በ4ቀናት ዉስጥ በእስለማዊ ታጣቂ ሀይሎች ወደ 30 የሚጠጉ ወታደሮች መገደላቸዉን ወታደራዊና ሚሊሻ ምንጮች ገልፀዋል ፡፡ ጥቃቱ በናይጄሪያ የሰሜን ምስራቅ ክፍልን ጨምሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፀጥታዉ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ያስመሰከረ ነዉም ተብሏል ፡፡
በአራቱ ቀናት በተፈፀመዉ ጥቃት 27 የመንግስት ወታደሮችና በአክራሪ እስላሞች አካባቢያቸዉን ለመታደግ ከተቋቋመዉ (ሲጄቲኤፍ ) ከተሰኘዉ የሲቪል ጥምረት ግብረ ሀይል ሃላፊዉን ጨምሮ 10 አባላቶች ህይወታቸዉ ማለፉን ሮይተርስ ምንጮቼ ነግረዉኛል ብሎ ዘግብዋል ፡፡ የሰራዊቱም ሆነ የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ቃል አቀባዮች እስካሁን ድረስ ምንም አይነት አስተያየት እንዳልሰጡበት ነዉ የተነገረዉ ፡፡
የእስላማዊ መንግስት የምዕራብ አፍሪካ አዉራጃ በሰሜን ምስራቅ በቦርኖ ግዛት የአካባቢዉ አስተዳደር ዋና ከተማ በሆነችዉ ሞንጎኖ በደረሰዉ ጥቃት 33 ወታደሮች ሲገደሉ አንድ ወታደር ደግሞ በቁጥጥር ስር ዉልዋል ሲል ገልጽዋል ፡፡ ሲጄቲኤፍ ከተሰኘዉ ጥምረትና ከሁለት ወታደራዊ ምንጮች እንደተገኘዉ መረጃ ደግሞ በሞንጎኖና በኩዋካ መካከል በተካሄደዉ ጥቃት 4 የጥምረቱ ተዋጊዎችና 15 የሚሆኑ ወታደሮች ህይወታቸዉ ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ የት እንደገቡ እንዳልታወቀ ነዉ የገለፁት ፡፡