loading
ፈረንሳይ በማሊ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት 19 ያልታጠቁ ንፁሃን መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ!

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምርመራ ቡድን እንዳረጋገጠው ፣ ባለፈው ጥር ወር ፈረንሳይ በማዕከላዊ ማሊ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት 19 ንፁሃንን ገድላለች፡፡ በተ.መ.ድ በማሊ ልዑክ እንዳስታወቀው ከሣተላይት በተገኙ ምስሎችና ከ 400 በላይ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ በመስራት የተዘጋጀ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ፈረንሳይ ሪፖርቱን አስተባብላለች፡፡ በማሊ በ 2012 ሰሜናዊ ክፍል የጂሃዲስቶች ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ከማሊ በተጨማሪ በጎረቤት ቡርኪናፋሶና ኒጀር ቀውሱ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ፈረንሳይ የቀድሞ የማሊ ቅኝ ገዢ ስትሆን ከ 2013 አንስቶ በማሊ ቀውስ መረጋጋት እንዲመጣ 5100 ወታደሮቿን አስፍራለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *