loading
ጥቁር ቆዳ ቀለም ያለዉ አንድ ሰዉ በፖሊሶች በግፍ ከተገደለ በኋላ በሚኒያ ፖሊስ አቅራቢያ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀጣጠሉ፡፡

አዲስ አበባ፣  ሚያዚያ ፡ 04፣ 2013 ጥቁር ቆዳ ቀለም ያለዉ አንድ ሰዉ በፖሊሶች በግፍ ከተገደለ በኋላ በሚኒያ ፖሊስ አቅራቢያ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀጣጠሉ፡፡ በአሜሪካ ብሩክሊን ማእከል ውስጥ የትራፊክ ማቆሚያ አካባቢ ፖሊሶች ጥቁር ቀለም ያለዉን አንድ ሰዉ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተኩሰው ከገደሉ በኋላ የተቃውሞ ሰልፎች በሚኒያፖሊስ አቅራቢያ መካሄዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሟች ዱዋንት ራይት የ20 ዓመት ወጣት መሆኑን ዘመዶቹ የተናገሩ ሲሆን የብሩክሊን ማዕከል ከንቲባ ከጥቃቱ በኃላ ከተማ አቀፍ ስዓት እላፊ በማወጅ ሁሉም ወደየቤታቸው እንዲሄዱና እንዲረጋጉ አዝዘዋል። የሚኒሶታ አስተዳዳሪ ቲም ዋልዝ ደግሞ ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተልኩ ነው በማለት ለራይት
ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡ በብሮክሊን ሴንተር በሚገኘው የፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ውጭ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የዱዋንት ራይት ስምን በተደጋጋሚ እየጠሩ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጭስና ሌሎች ቁሳቁሶች በመኮንኖች ሲተኮሱ የሚያሳይ ምስልም ከስፍራው እየወጣ ይገኛል፡፡ የብሮክሊን ማእከል ፖሊስ መምሪያ በሰጠው መግለጫ እሁድ ከሰዓት በኋላ ሟች የትራፊክ ጥሰት መፈፀሙንና ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ለመዋል በሚሞክሩበት ጊዜ ወደ መኪናው በመግባት ሊያመልጥ ሲል አንድ ፖሊስ ተኩስ መክፈቱን ገልፀዋል፡፡ ራይት ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር ከመጋጨቱ እና መከለያዎችን ከመጣሱ በፊት በጥይት እንደተመታና በሰዓቱ ህይወቱ ማለፉም ተነግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *