loading
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በድብቅ ጋብቻ መፈጸማቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23፣ 2013 የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በድብቅ ጋብቻ መፈጸማቸው ተሰማ:: ይህ ጋብቻ ለቦሪስ ጆንሰን ሦስተኛቸው ሲሆን ለባለቤታቸው ሲሞንድስ የመጀመሪያቸው ነው የ56 ዓመቱ የብሪታንያ (ዩኬ) ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ከ33 ዓመቷ ካሪ ሲሞንድስ ጋር በዛሬው ዕለት በዌስትሚንስትር ባለው ቤተክርስቲያን በድብቅ ጋብቻ መመስረታቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ጋብቻው በድብቅ የጠቅላይ ሚንስትሩ እና ባለቤታቸው የቅርብ ወዳጆች እና ቤተሰቦች ባሉበት መፈጸሙን የቦሪስ ጆንሰን የካቢኔ አባላት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ገልጸዋል። ጋብቻው ከተፈጸመ ከሰዓታት በኋላ ዘግይተውም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ባለቤታቸው የጋብቻ
ፎቶአቸውን ለቀዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጋር ጋብቻ የፈጸሙት ሲሞንድስ ከአንድ ዓመት በፊት ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ሆስፒታል በገቡበት ተመሳሳይ ወቅት ከጠቅላይ ሚኑስትሩ የመጀመሪያ ልጃቸውን በሆስፒታል ተገላግለዋል ተብሏል።

ባሳለፍነው ዓመት ሊጋቡ ቀነ ቀጠሮ ይዘው የነበሩት ሁለቱ ጥንዶች ጋብቻቸውን በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ሳያራዝሙት እንዳልቀሩ ነው የተገመተው።  ጆንሰን ከዚህ ቀደም ከነበራቸው የትዳር ህይወት ቢያንስ 5 ልጆችን እንዳፈሩ ይነገራል፡፡ የ56 ዓመቱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ከ25 ዓመት በፊት ማሪና ዊለር ከተሰኙ ባለቤታቸው ጋር ጋብቻ ፈጽመው በ2018 ፍቺ እስከፈጸሙበት ጊዜ ድረስ 4 ልጆችን መውለዳቸው ተሰምቷል።

የአሁኗ ባለቤታቸው ሲሞንድስ ፣ ቦሪስ ጆንሰን የለንደን ከንቲባ ሆነው እንዲመረጡ እና ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን እንዲመጡ የፖለቲካ ዘመቻዎችን በመምራት ውጤታማ ስራ እንደሰሩላቸው ተጠቁሟል። ከዚህ ቀደም በጠ/ሚኒስትርነት ኃላፊነት ላይ እያሉ ትዳር የመሰረቱ የመጨረሻው የብሪታንያ መሪ
ሎርድ ሊቨርፑል ናቸው ሎርድ ሊቨርፑል ፣ እ.ኤ.አ. በ1822 ፣ ከዚህ ቀደም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ላይ እያሉ ትዳር የመሰረቱ የመጨረሻው የብሪታንያ መሪ ናቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *