loading
የሴናተር ጂም ኢንሆፍ ጉብኝት ለኢትዮ-አሜሪካ ዲፕሎማሲ ያለዉ ፋይዳ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013  የሴናተር ጂም ኢንሆፍ ጉብኝት ወቅታዊውን የኢትዮ-አሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሊያለዝበው ይችላል ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር በዕውቀቱ ድረሰ ተናገሩ፡፡ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉን ባስታወቀ ማግስት ድርጊቱን የኦክላሃማው ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡

ሴናተሩ በሀገራቸው ሳሉ ከሚያሳዩት የኢትዮጵያ አጋርነት ሌላ ከሰሞኑ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ መግባታቸዉ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ለሻከረዉ የሁለቱ ሀገራት ግኑኝንት መሻሻል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ሴናተሩ ኢትዮጵያን በሚገባ ከማወቃቸው ጋር ተያይዞ የችግሩን ምንጭ ስለሚረዱ የባይደን አስተዳደር የጣለውን የጉዞ እገዳ ማዕቀብ መቃወማቸው እና ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች ጋር መወያየታቸው ደግሞ ነባራዊ ሁኔታውን በሚገባ ለመረዳት ያግዛቸዋል ነው ያሉት፡፡ እናም የሀገራቱን ግንኙነት ለማሻሻል አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ መንግሥት እንደ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ሌሎችን መሳብ እና እውነታውን ማሳየት  ይገባዋል፤ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን በእውቀት እና በጥበብ መምራት ይጠበቅበታል፤ በግለሰቦች እና በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችን በመዋቅራዊ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ መምከራቸዉን አሚኮ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *