loading
የአገዛዝ እንጂ የፖሊሲ ለዉጥ አንፈልግም -ሱዳናዊያን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013  በሱዳን የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ መንግስት ይቀየር ወደሚል አጀንዳ መሸጋገሩ ተሰማ፡፡ ሱዳን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ምክረ ሀሳብን ተቀብላ ተግባራዊ ያደረገችው የኢኮኖሚ መሻሻያ የፈጠረው የዋጋ ንረት ነው በሀገሪቱ ህዝባዊ አመፅ የቀሰቀሰው ተብሏል በተለያዩ የሱዳን ከተሞች በርካታ ሰዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስልጣኑን ይልቀቅ የሚል መፈክር ይዘው ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል ነው የተባለው፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በካርቱም ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞች እኛ የምንፈልገው የፖሊሲ ሳይሆን የአገዛዝ ለውጥ ነው የምንፈልገው ብለዋል፡፡
በሱዳን አመፁ የተቀሰቀሰው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ለሀገሪቱ ከፈቀደው ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ 90 በመቶ የሚሆነውን 50 ቢሊዮን ዶላር መልቀቁን ባስታወቀ ማግስት ነው ተብሏል፡፡

በተፈጠረው የኑሮ ውድነት ብስጭት የገባቸው ሰልፈኞች በካርቱም የፕሬዚዳንቱ ህንፃ ፊት ለፊት ቁሳቁሶችን ሲያቃጥሉና መንገዶች ሲዘጉ እንደነበር ዘገባው አክሎ አስነብቧል፡፡ በኡንዱርማንና ከሰላ ከተሞችም ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በአመፅ ከስልጣን ለማውረድ የሲታገሉ የተገደሉ የዲሞክራሲ አቀንቃኞች ጉዳይም ፍትህ እንዲያገኝ ጠይቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *