loading
የቀድሞ የአፋር ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በሱልጣን ሐንፈሬ አሊ ሚራህ የሚመራውና በስደት በውጭ አገራት ሲኖሩ የነበሩ ልኡካን ቡድን አባላት ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ፣ከአፋር ሰብዓዊ መብት አቶ ጋአስ አህመድ እና ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር አቶ ኡመር አሊሚራህ ይገኙበታል፡፡
ልኡካኑ አዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዲሪ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ስዩም አወል፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ በሽግግር መንግስቱ ወቅት የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩና በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደርም ሆነው አገራቸውን አገልግለዋል፡፡
በኋላ ላይ ከመንግስት ጋር በነበራቸው አለመግባባት ወደ ውጭ አገር በመሄድ በአሜሪካ በስድት እየኖሩ ነበር፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *