loading
ሙን ጃይ ኢን ደቡብና ሰሜን ኮሪያን በፍቅር ሀዲድ ሊያገናኙ ያስባሉ፡፡

የደቡብ ኮርያው ፕሬዝዳንት ለዓመታት በግጭት ውስጥ የቆዩትን ሴኡልና ፒዮንግያንግን የሚያገናኝ የባቡር መስመር ግንባታ ለማካሄድ እቅድ ይዘዋል፡፡
ምንም እንኳ በደቡብና ሰሜን ኮርያ መካከል የፖለቲካ ውህደት ለማድረግ ጊዜ የሚፈልግ ጉዳይ ቢሆንም በትራንስፖርት ቢተሳሰሩ ኢኮኖሚያቸውን ከማሳደግ አልፈው የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች እርስ በርስ እንዲቀራረቡ በር ይከፍታል ብለዋል ሙን ጃይ ኢን፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ተግባራዊ እንዲሆን ያሰቡት “ሬይልሮድ ኮሚዩኒቲ” የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት ደቡብ ኮርያን ከሌሎች የእስያ ሀገራት ጋርም በትራንስፖርቱ ዘርፍ ማስተሳሰር የሚችል ነው፡፡
ሙን ሊያስገነቡት ያሰቡት የባቡር መንገድ ሀገራቸውን ከቻይና፣ ከሞንጎሊያ፣ ከሩሲያና ከጃፓን ጋር የሚያገናኝ መስመር ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *