loading
አንጋፋው የትያትር ባለሞያ፣ አዘጋጅ እና ፀሐፊ ተውኔት ጌታቸው ደባልቄ አረፉ

አንጋፋው የትያትር ባለሞያ፣ አዘጋጅ እና ፀሐፊ ተውኔት ጌታቸው ደባልቄ አረፉ። በትናንትናው ምሽት ያረፉት አንጋፋው የትያትር ባለሞያ፣ አዘጋጅ እና ፀሐፊ ተውኔት ጌታቸው ደባልቄ ያረፉት በትናንትናው ምሽት በ83 ዓመታቸው ነው። ሸገር እንደዘገበው ቤተሰቦቻቸው የቀብር ሥነሥርዓቱ በነገው ዕለት እንደሚፈጸም ተናግረዋል። አርትስ ቲቪ  በአንጋፋው የትያትር ባለሞያ ጌታቸው ደባልቄ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ የትያትር ወዳጆች መፅናናትን […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስዊዲን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስዊዲን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስዊዲን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ማርጎት ቫለርስትሮም ጋር ዛሬ ጠዋት ተገናኝተው ተወያይተዋል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ዘግቧል፡፡ ሁለቱ ወገኖች በኢትዮ ስዊዲን ትብብር ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን ቫለርስትሮም ስዊዲን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በድጋሜ አረጋግጠዋል ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  በኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ ናቸው

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  ጀምሮ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት  ጉብኝት ያደርጋሉ የኬንያው ፕሬዝዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  ጀምሮ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት  የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በሁለቱ አገሮች መካከል ለዘመናት የቆየውንና በሁኔታዎች የማይለዋወጠውን ታሪካዊ ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል። ኡሁሩ ኬንያታ የአፍሪካ አባት በመባል የሚታወቁት የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት  ጄሞ ኬንያታ […]

ፖሊስ የዓድዋ ድል ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቄያለሁ አለ  

ፖሊስ የዓድዋ ድል ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነገ በአዲስ አበበ ከተማ የሚከበረውን የዓድዋ ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ማድረጉን በው ያስታወቀው። በበዓሉ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ በቂ ዝግጅት ማደረጉንም ገልጿል፡፡ በበዓሉ ማንኛውም ዓይነት ሁከት በሚፈጥር አካል […]

ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ

ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በመጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከማሊ አቻው ጋር ላለበት ጨዋታ 33 ተጫዋቾች በዕጩነት የተመረጡ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ተጫዋቾቹ የካቲት 26/2011 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚገኘው የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተገኝተው ሪፖርት […]

የዓድዋ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማዋ ጸጥታ ምክር ቤት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ

የዓድዋ ድል በዓል በደማቅና ሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ገለጸ፡፡ የፀጥታ ምክርቤቱ የዓድዋ ፌስቲቫል እና የዓድዋ ድል በዓል አከባበርን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከተወያየ በኋላ መግለጫ አውጥቷል። በዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል ከ500 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ያለው መግለጫው ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር እና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ዝግጅት በሙሉ ማጠናቀቁንም አስታውቋል፡፡ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አንደሚያመለክተው በዕለቱ በዓሉን ለሚያከብሩ የከተማዋ ነዋሪዎች የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት በነፃ አገልግሎት ይሰጣል።