loading
አዲስ የተሾሙ የክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር የጀመረዉን የለዉጥ ጉዞ ለማፋጠን እስከ ክፍለ ከተማ መዋቅሩን በአዳዲስና ብቁ አመራሮች እያደራጀ ነዉ ። በዚህ መሠረት የክፍለከተሞቹ ምክርቤቶች ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አዳዲስ ስራ አስፈፃሚዎችን ሹመት ማጽደቁን ከንቲባ ጽህፈት ቤት ገልጻል፡፡አራዳ ክፍለ ከተማ ወ/ሮ አበባ እሸቴ፣ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፣ ወ/ሮ ህይወት ጉግሳ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ልደታ ክፍለ ከተማ አቶ አለማው ማሙዪ […]

ምናንጋግዋ ሀገሬን በ2030 ከድህነት አላቅቃታለሁ አሉ፡፡

የዚምባቡየው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አወዛጋቢውን የምርጫ ውጤት በአሸናፊነት አጠቃለውታል፡፡ አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ምናንጋግዋ ከ37 ዓመት ወዲህ የሀገሪቱ የመጀመሪያው በምርጫ ወደ ስልጣን የመጡ መሪ በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡ ምርጨውን አጭበርብረዋል ተብለው በተፎካካሪያቸው ወቀሳ የደረሰባቸው ፕሬዝዳንቱ አሁን በጋራ ሀገራችንን የምናሳድግበት ወቅት ስለሆነ አንድነታችንን እናጠናክር የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ምናንጋግዋ በሚቀጥሉት 11 ዓመታት ውስጥ ከድህነት የተላቀቀች፣ ህዘወቦቿ መካከለኛ […]

ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ነሃሴ 17 እና 18 ቀን 2010 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በብአዴን 12ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ረቂቅ ሪፖርትና ለጉባዔው በሚቀርቡ ሌሎች ወቅታዊና መደበኛ ጉዳዮች ላይ ተወያቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ባለቤትነት በሀገር ደረጃና ብአዴን በሚመራው የአማራ ክልል የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ […]

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአዲሱ ክትባት ሁለት ሰዎች ከኢቦላ ቫይረስ ነጻ ሆነዋል::

  በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ክትባት ውጤት እያሳየ መምጣቱን የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አታውቋል፡፡ በቫይረሱ ተይዘው የሙከራ ክትባቱን ሲወስዱ የነበሩ ሁለት ሰዎች ከበሽታው ነጻ ሆነው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ መደረጉን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው ሁለቱ ሰዎች በተሰጣቸው ህክምና መዳናቸውን ተከትሎ ዓለማችን […]

የማይናማር የጦር ጀኔራሎች በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊጠየቁ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባደረኩት ምርመራ በማይናማር የሮሂንጊየያ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ዘር ማጥፋትን ያለመ እንደሆነ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡ ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው ለተፈጸመው ወንጀል ቀጥተኛ ትእዛዝ በመስጠት እጃቸው አለበት የተባሉት የሀገሪቱ የመከላከያ አዛዥና አምስት ሹሞቻቸው በህግ ፊት ቀርበው መጠየቅ አለባቸው ብሏል ድርጅቱ ፡፡ ድጅቱ በሪፖርቱ እንዳስታወቀው የማይናማር ወታደሮች በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸሙት የግድያና በርካታ መንደሮችን በጅምላ […]

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በአዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ፋና እንደዘገበዉ አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በቁጥጥር ስር የዋሉት በዛሬው እለት አዲስ አበባ አትላስ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው እለት ባካሄደው አስቸኳይ የአቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት ከአቶ አብዲ በተጨማሪ የ6 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብትን አንስቷል።      

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተፈቅዶላታል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንዳሉት ድጋፉ በቀጥታ የሀገሪቱን በጀት የሚደግፍ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዓለም ባንክን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት  በ97 በኢትዮጵያ በተካሄደው ምርጫ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ለቀጥታ በጀት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርገው አያውቁም፡፡ ለገንዘቡ መገኘት አሁን በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ ዋኛው ምክንያት መሆኑንም ዶክተር አብይ ተናግረዋል፡፡ የዓለም ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ጂም ያንግ ኪም በበኩላቸው […]