loading
በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ በላይ መድረሱ ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ በላይ መድረሱ ተነገረ፡፡ በአህጉሩ የተመዘገበው የሟችና የታማሚዎች ቁጥር ከቀሪው ዓለም ጋር ሲነፃፀር አናሳ ቢሆንም የበሽታው ስርጭት ከነበረበት በፍጥነት እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡ በተለይ በአፍሪካ ሁለተኛው ዙር የወረርሽኝ መስፋፋት መከሰቱን ተከትሎ ሆስፒታሎች በሽተኞችን መቀበል እስኪያቅታቸው መጨናነቃቸው ነው የሚነገረው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በአፍሪካ በሽታው ከታየ ጀምሮ እስካሁን ድረስ […]

የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልመጅድ ቲቦኒ የሀገሪቱን ፓርላማ በትነው አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልመጅድ ቲቦኒ የሀገሪቱን ፓርላማ በትነው አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አልጄሪያ የሰማእታት ቀንን በምታከብርበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡ ቲቦኒ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት የተለያዩ የፓርቲ መሪዎች ጋር ተደጋጋሚ ስብሰባዎችና ምክክሮችን ካደረጉ በኋላ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕሬዚዳንቱና የካቢኔ አባሎቻቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ […]

በዲሞክራቲክ ኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር በጉዞ ላይ እያሉ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 16፣ 2013 በዲሞክራቲክ ኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር በጉዞ ላይ እያሉ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸው ተሰማ:: አምባሳደር ሉካ አታናሲዮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተሸከርካሪ በሚጓዙበት ወቅት ነው ከግል ጠባቂያችው ጭምር ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው የተገደሉት፡፡ አምባሳደሩን እና አጃቢያቸውን ሲያጓጓዝ የነበረውና የሀገሬው ተወላጅ የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅት ሾፌርም በደረሰው ጥቃት ተገድሏል ነው የተባለው፡፡ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት […]

የናይጄሪያ ታጣቂ ቡድኖች አግተዋቸው የነበሩት 53 ሰዎችን ለቀቁ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 16፣ 2013 የናይጄሪያ ታጣቂ ቡድኖች አግተዋቸው የነበሩት 53 ሰዎችን ለቀቁ:: የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት ማረጋገጫ ኒጀር ውስጥ በታጣቂዎቹ በእገታ ስር ከነበሩ ሰዎች መካከል 20 ሴቶችንና 9 ህፃናትን ጨምሮ 53ቱም ተለቀዋል፡፡ ሰዎቹ በታጣቂዎቹ ታፍነው የተወሰዱት ባለፈው ሳምንት በአውቶቡስ በሚጓዙበት ወቅት እንደነበር ተነግሯል፡፡ የኒጄር መንግስት ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ ታጋቾቹ በተቻለ ፍጥነት እንዲለቀቁ አስፈላጊው ድርድር ተደርጓል […]

ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሀገሯ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከመንግስ እውቅና ውጭ ከዋና ከተማዋ እንዳይወጡ ከለከለች፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣ 2013 ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሀገሯ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከመንግስ እውቅና ውጭ ከዋና ከተማዋ እንዳይወጡ ከለከለች፡፡ ሀገሪቱ በዲፕሎማቶች ላይ ይህን እገዳ የጣለችው ሰሞኑን ለጉብኝት ከከተማ ውጭ ሲጓዙ የነበሩት የጣሊያኑ አምባሳደር መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ማንኛውም የዲፕሎማቲክ ሚሽን አባላት ከዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ለመውጣት ሲፈልጉ ቀድመው ለመንግስት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺኬሴዲ ከዚህ […]

በአፍሪካ ለኮቪድ-19 ታካሚዎች ከፍተኛ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ እጥረት አለ ተባለ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 24፣ 2013 በአፍሪካ ለኮቪድ-19 ታካሚዎች ከፍተኛ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ እጥረት አለ ተባለ:: የኮሮናቫይረስ በአፍሪካ አህጉር ከተከሰተ ጀምሮ መካለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት አቅምን ያገናዘበ አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ እጥረት ትልቅ ፈተና መሆኑ ነው የሚነገረው፡፡ በአሁኑ ወቅት በታዳጊ ሀጋራት የሚገኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በየቀኑ የኦክስጅን ድጋፍ እንደሚፈልጉ አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ የኦክስጅን እጥረት በበርካታ […]

በህዳሴው ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል ሂደት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያሉ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 በህዳሴው ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል ሂደት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያሉ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡ የውይይቱ ዓላማ በግድቡ ዙሪያ በእውነታ ላይ የተመሰረተና ትክክለኛ መረጃን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስተላለፍ ነው ተብሏል፡፡ ውይይቱ በዌብናር የተካሄ ሲሆን በውይይተቱ ከተሳተፉት መካከል በሀገር ውስጥና በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም አሜሪካዊያን ይገኙበታል፡፡ ተወያዮቹ በዋናነት […]

በኢኳቶሪያል ጊኒ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ በደረሰ ፍንዳታ 20 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 በኢኳቶሪያል ጊኒ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ በደረሰ ፍንዳታ 20 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ በወታደራዊ ካምፑ ላይ አራት ከፍተኛ ፍንዳታዎች መድረሳቸው የታወቀ ሲሆን ከሞቱት 20 ሰዎች በተጨማሪ 600 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡ ፍንዳታው የደረሰው የኢኮኖሚ ከተማ በሆነችው ባታ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ንኮማ ንቶማ ወታደራዊ ካምፕ ነው፡፡ የፍንዳታው መንስኤ በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች […]

የኒጄሩ ፕሬዚዳንት ማማዱ ኢሱፎ የ2020 የሞ ኢባራሂም ሽልማት አሸነፉ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 30፣ 2013 የኒጄሩ ፕሬዚዳንት ማማዱ ኢሱፎ የ2020 የሞ ኢባራሂም ሽልማት አሸነፉ:: ኢሱፉ ሽልማቱን ያገኙት በሀገራቸው የተከሰቱ በርካታ ችግሮች በቁርጠኝነት በመጋፈጥ ለህዝባቸው ጠቃሚ ስራ ሰርተዋል በሚል ነው፡፡ በተለይ በኒጄር ነፍጥ አንግበው ሽብር የሚፈጥሩ ሀይሎችን በመዋጋት፣ በርሃማነትን በመከላከል የልማት ስራዎችን በመስራት ረገድ አመርቂ ውጤት አስገኝተዋል ነው የተባለው፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሱፉ ሀገራቸውን ለ10 ዓመት ካገለገሉ በኋላ ስልጣናቸውን […]

በናይጄሪያ 30 ወታደሮች በእስላማዊ ታጣቂ ሀይሎች መገደላቸዉ ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 በናይጄሪያ 30 ወታደሮች በእስላማዊ ታጣቂ ሀይሎች መገደላቸዉ ተሰማ:: በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ በ4ቀናት ዉስጥ በእስለማዊ ታጣቂ ሀይሎች ወደ 30 የሚጠጉ ወታደሮች መገደላቸዉን ወታደራዊና ሚሊሻ ምንጮች ገልፀዋል ፡፡ ጥቃቱ በናይጄሪያ የሰሜን ምስራቅ ክፍልን ጨምሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፀጥታዉ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ያስመሰከረ ነዉም ተብሏል ፡፡ በአራቱ ቀናት በተፈፀመዉ ጥቃት 27 […]