loading
በሀገር ደረጃ የሚሰራ የፎረንሲክ ማዕከል ባለመኖሩ አስቸኳይ ዉሳኔ የሚያስፈልጋቸዉን ጉዳዮች ቶሎ መርምሮ ለማወቅ እንቅፋት እየሆነ ነዉ ፡፡

በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የፎረንሲክ ሜዲስን ቴክኖሎጂ ሃላፊ ዶክተር እንየዉ ደባሽ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት የቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የአስክሬን ምርመራ ፤የእድሜና የፆታ ጥቃት ሲደርስ በፎረንሲክ ክፍሉ ምርመራ ቢያደርግም፤ ከአባትነትና ከእናትነት ማረጋገጫ መሰል ዝርዝር የምረዛ ችግሮች ሲኖሩ ከሀገር ዉጪ ናሙና በመላክ ምርመራ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በፎረንሲክ ምርመራ ባለሞያዎችን ወደ ህንድ በመላክ ለማሰልጠን ቢቻልም አገልግሎቱን በተገቢና በተቀላጠፈ መልኩ ለመስጠት መመርመሪያ […]

በጅግጅጋ ከተማ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት የተላከው የጤና ባለሙያዎች ቡድን ትላንት ሀምሳ ዘጠኝ ለሚደርሱ ተጎጂዎች የህክምና እርዳታ አደረገ፡፡

ከታካሚዎች ዉስጥም ሰላሳ የሚሆኑት ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ናቸው ። ከነዚህ ዉስጥም ዘጠኝ ለሚሆኑ ተጎጂዎች ቀዶ ጥገና የተደረገ ሲሆን የተቀሩት በዛሬ እለት የቀዶ ጥገና ህክምና እርዳታ ይደረግላቸዋል ተብሏል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ለጤና ባለሙያዎቹ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት በትንሽ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) መድሃኒት የማድረስ ስራ ይጀመራል፡፡

መድሃኒት የማድረስ ስራው ሳይንስ እና ቴክኖሎጄ ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንደሚሰሩት የሳይንስና ቴክኖሎጄ ሚኒስቴር በድረ ገፁ ላይ አስፍሯል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ አመት በትምህርት፤ በጤና በግብርናና በሌሎች ዘርፎች የተሻለ ስራን ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ለመስራት በሚያስችለው ሁኔታ ላይ ከሰራተኞቹ ጋር መክሯል፡፡

ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በጅግጅጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 128 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጡ፡፡

የህክምና ቡድን መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ትላንት አመሻሽ ላይ ከጅግጂጋ ሲመለሱ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ቡድኑ በስምንት ቀን ቆይታው ለ128 ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና አገልግሎት ድጋፍ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ከተጎጅዎቹ መካከልም ግማሽ ያህሎቹ የጭንቅላት፣ የደረት፣ የሆድና የደረት ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ የህክምና ቡድኑ ወደ ጅግጂጋ ከማቅናቱ በፊትም በድሬዳዋ ከተማ […]

የዓለም የጤና ድርጅት የዲሞክራቲክ ኮንጎ ጉዳይ አሳስቦኛል ብሏል፡፡

በሀገሪቱ የተፈጠረው አለመረጋጋት የኢቦላ ቫይረስን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት አደጋ ላይ ጥሎታል ነው ያለው ድርጅቱ፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡ ዶክተር ቴዎድሮስ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተፋላሚ ሀይሎች በአስቸኳይ ተኩስ አቁመው የጤና ባለሞያዎች እንደልባቸው ቫይረሱ ወደተከሰተበት አካባቢ ተንቀሳቅሰው ስራቸውን እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ […]

የተሽከርካሪ አደጋ አስከፊ እየሆነ በቁጥርም እያሻቀበ ነው፡፡

በአገራችን 2010 ዓ.ም 40ሺህ 998 የተሸከርካሪ አደጋ ደርሷል፡፡ 5ሺህ 118 ሰዎች በተሸከርካሪ አደጋ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፡፡ 7ሺህ 754 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 7ሺህ 775 ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከ 920 ሚሊዮን 771 ሺህ ብር በላይ የተገመተ ንብረት ወድሟል፡፡ ባለፈው ዓመት 2009ዓ.ም የደረሰው አደጋ 38ሺህ 737 ነበር፡፡ አቶ ይግዛው ዳኘው የትራንስፖርት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት […]

የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ማሻሻያ ተደረገበት፡፡

በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ባለስልጣኑ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ላይ ብቻ እንዲያተኩርና ቀደም ሲል በባለስልጣኑ ይሰጡ የነበሩ ሌሎች አገልግሎቶች ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት እንዲዛወሩ መደረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በቲዉተርና በፌስቡክ ገጻቸዉ አስታዉቀዋል፡፡ በቀጣይም የስራ ኃላፊዎች፣ሰራተኞችና የአሰራር ስርዓቱ ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን በማለት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በተያዘው አቅጣጫ መሰረት […]

አርሷደሯ ጌሪ አሜሪካ ተብሎ ለሚጠራው የእህል ፈጅ ትል መድሀኒት አገኙ፡፡

አርሷደሯ ወ/ሮ ታቦቴ አባተ በቦኖ በደሌ ዞን አርሶ አደር ናቸው። ከችግራቸው በመነሳትም ጌሪ አሜሪካ ለተባለ ትል አዲስ የትል ማጥፊያ ፈጥረዋል። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ሴንተር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ጌሪ አሜሪካ በቆሎን በብዛት የሚያጠቃ ትል ነው።ትሉ ቁጥጥር ካልተደረገበት በበቆሎ ምርት ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል። በአንድ ሌሊት በ1500 እጥፍ ሊራባ ይችላል። ወ/ሮ ታቦቴ ታዲያ ይህን ትል የሚገድል መድሀኒት […]

ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች የካንሰር መከላከያ ክትባት በጥቅምት ወር መሰጠት ሊጀመር ነው፡፡ 

በአገር አቀፍ ደረጃ ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች በመደበኛነት የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባትን ከጥቅምት 2011 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማትና በሚዘጋጁ ጊዜያዊ የክትባት ማዕከሎች ሊሰጥ መሆኑን የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በድረገጹ አስታዉቋል፡፡ የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካይ አቶ አስናቀ ዋቅጅራ የማህጸን በር ካንሰር በሽታ በአገራችን ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በስፋት በወሊድ ዕድሜ ክልል የሚገኙ […]