loading
ኒው ዚላንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ አለማስመዝገቧን ተከትሎ ክልከላዎችን በሙሉ ልታነሳ ነው ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 ኒው ዚላንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ አለማስመዝገቧን ተከትሎ ክልከላዎችን በሙሉ ልታነሳ ነው ::የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን በሀገራቸው ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች እንዴሌሉ ተናግረው ከእንግዲህ አካላዊ መራራቅን እንጅ እንቅስቃሴን አንገድብም ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ ከውጭ የሚገቡ ዜጎቻችን ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ማድረግ የግድ ይላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ለተገኘው ውጤት ሁሉንም ዜጎቻቸውን […]

ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::የብግብፅ የህክምና ማህበር በሰጠው መግለጫ የሀገሪቱ የጤና አጠባበቅ ስርዓት በፍጥነት ካልተስተካከለና ለሀኪሞች ልዩ እንክብካቤ ካልተደረገላቸው የበለጠ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ብቻ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሰባት ዶክተሮች መሞታቸው ሁኔታው ምን ያህል አደገኛ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል ነው የተባለው፡፡ ከሁለት […]

ኬንያዊያን ፖሊስ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ ያቁም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ኬንያዊያን ፖሊስ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ ያቁም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው:: በኬንያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተጣለውን የእንቅስቃሴ እገዳ ተከትሎ ፖሊስ ህግ በማስከበር ሰበብ በርካታ የሰብዓዊ መብቶችን እየጣሰ እንደሆነ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው መንግስት እገዳውን ከጣለ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል በተከሰቱ ግጭቶች ከ15 ያላነሱ […]

የኮሮና ቫይረስ  በ164 ሰዎች ላይ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012  የኮሮና ቫይረስ  በ164 ሰዎች ላይ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 670 መድረሱንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው […]

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 16 ሚሊየን ከፍ አለ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 16 ሚሊየን ከፍ አለ::በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 16 ነጥብ 5 ሚሊየን ከፍ ማለቱን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የ2020 የሰብዓዊት እርዳታ ፍላጎቶች ላይ ክለሳ […]

ብራዚል በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሟች ዜጎቿ ቁጥር በዓለም ሁለተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል

አዲስ አበባ፣ሰኔ 7፣2012 ብራዚል በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሟች ዜጎቿ ቁጥር በዓለም ሁለተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል:: ደቡብ አሜሪካዊቷ ሃገር ብራዚል ዓርብ ዕለት በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥርን ከፍ በከፍተኛ መጠን የመዘገበች መሆኑን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃን ከአውሮፓዊቷ እንግሊዝ ተረክባለች፡፡ ይሄንን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት የሀገሪቱ የጤና ስርዓት ትልቅ ጫና ውስጥ ይገኛል ብሏል፡፡የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ዓርብ ዕለት የ24 […]

የሶማሊያው አልሻባብ የኮሮና ቫይረስ ማከሚያ ማዕከልን አቋቁመ::

አዲስ አበባ፣ሰኔ 7፣2012 የሶማሊያው አልሻባብ የኮሮና ቫይረስ ማከሚያ ማዕከልን አቋቁመ:: ሶማሊያ ላይ የመሸገው ፅንፈኛው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን፤ በሀገሪቱ ውስጥ የኮቪድ-19 ሕክምና ማዕከል ማቋቋሙን ገልፆ፤ የዓለም አቀፍ የጤና ባለሥልጣናትን ትንበያ በመጥቀስ በሽታው ከባድ ስጋት እንዳስከተለ ገልጧል ፡፡ ታጣቂ ቡድኑ መልዕክቶችን በሚያስተላልፈበት የአንዳሉስ ራዲዮ ስርጭት አል- ሸባብ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና እንክብካቤ ኮሚቴ በማቋቋም የኮቪድ-19 ማዕከል መገንባቱን […]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸዉ 75 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸዉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸዉ 75 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸዉ ተገለጸ፡፡ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ዉ 5 ሺ 6 መቶ 36 የላብራቶሪ ምርመራ አንድመቶ ሰባስድስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸዉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ አስታዉቀዋል፡፡በአጠቃላይም በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 5 መቶ 21 ደርሷል፡፡ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች […]

በኒው ዚላንድ ከ24 ቀናት በኋላ ሁለት የኮሮሮናቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 በኒው ዚላንድ ከ24 ቀናት በኋላ ሁለት የኮሮሮናቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸው ተሰማ:: ቢቢሲ በዘገባው እንዳስነበበው ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይረስን አጥፍቻለሁ ካለች በኋላ ነው ከእንግሊዝ በመጡ ሁለት ሰዎች ቫይረሱ የተገኘው፡፡ ኒው ዚላንድ ባለፈው ሳምንት አዲስ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች አለመገኘታቸውን ተከትሎ በሀገር ውስጥ ጥላቸው የነበሩትን የዕንቅስቃሴ እገዳዎች ሙሉ በሙሉ አንስታለች፡፡ አሁን ላይ ከእንግሊዝ በልዩ ፈቃድ ወደ […]

ብራዚል ኮሮናቫይረስ ከቁጥጥሬ ውጭ አይደለም ብትልም በቀን ውስጥ የሚመዘገበው የሟችና የታማሚ ቁጥር እያሻቀበ ነው::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  ብራዚል ኮሮናቫይረስ ከቁጥጥሬ ውጭ አይደለም ብትልም በቀን ውስጥ የሚመዘገበው የሟችና የታማሚ ቁጥር እያሻቀበ ነው:: የፕሬዚዳት ዣየር ቦልሶናሮ የፅህፈት ቤት ሀላፊ ዋልተር ብራጋ ኔቶ በሰጡት መግለጫ በሀገራችን ኮቪድ 19 ቀውስ ፈጥሮብናል ግን ደግሞ ከቁጥጥራችን አልወጣም ማለታቸው ብዙዎቹን አስገርሟል ነው የተባለው፡፡ ምክንያቱም ሀላፊው ይህን አይነት መግለጫ የሰጡት በብራዚል በ24 በሰዓታት […]