loading
አንጋፋው የትያትር ባለሞያ፣ አዘጋጅ እና ፀሐፊ ተውኔት ጌታቸው ደባልቄ አረፉ

አንጋፋው የትያትር ባለሞያ፣ አዘጋጅ እና ፀሐፊ ተውኔት ጌታቸው ደባልቄ አረፉ። በትናንትናው ምሽት ያረፉት አንጋፋው የትያትር ባለሞያ፣ አዘጋጅ እና ፀሐፊ ተውኔት ጌታቸው ደባልቄ ያረፉት በትናንትናው ምሽት በ83 ዓመታቸው ነው። ሸገር እንደዘገበው ቤተሰቦቻቸው የቀብር ሥነሥርዓቱ በነገው ዕለት እንደሚፈጸም ተናግረዋል። አርትስ ቲቪ  በአንጋፋው የትያትር ባለሞያ ጌታቸው ደባልቄ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ የትያትር ወዳጆች መፅናናትን […]

የዓድዋ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማዋ ጸጥታ ምክር ቤት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ

የዓድዋ ድል በዓል በደማቅና ሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ገለጸ፡፡ የፀጥታ ምክርቤቱ የዓድዋ ፌስቲቫል እና የዓድዋ ድል በዓል አከባበርን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከተወያየ በኋላ መግለጫ አውጥቷል። በዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል ከ500 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ያለው መግለጫው ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር እና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ዝግጅት በሙሉ ማጠናቀቁንም አስታውቋል፡፡ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አንደሚያመለክተው በዕለቱ በዓሉን ለሚያከብሩ የከተማዋ ነዋሪዎች የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት በነፃ አገልግሎት ይሰጣል።  

በነጻ ትምህርት ዕድል ሰበብ  ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ችግር እየገጠማቸው ነው ተባለ

በነጻ ትምህርት ዕድል ሰበብ  ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ችግር እየገጠማቸው ነው ተባለ። እስካሁን 47 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቻይና ውስጥ ታስረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ዜጎች ያለበቂ መረጃና ፈቃድ ወደ ቻይና በመሄድ ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም ዋናው ምክንያት በህገወጥ ደላሎች በኩል የሚነዛው የተሳሳተና የተጭበረበረ የነጻ የትምህርት ዕድል ቅስቀሳ […]

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጥቶላቸዋል

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጥቶላቸዋል በዕጣ ከተላለፉ ቤቶች ውስጥም 32 ሺህ 653 ቤቶች በ20/80 ፕሮግራም የተካተቱ ሲሆን ቀሪዎቹ 18 ሺህ 576 ደግሞ የ40/60 ቤቶች ናቸው። በዚህም መሰረት በዕጣ ከተላለፉ የ20/80 ፕሮግራም ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 248 ስቲዲዮ፣ 18 ሺህ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7 ሺህ 127 ባለ […]

በኢትዮጵያ ዘላቂ የከተሞች ዕድገት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ ዘላቂ የከተሞች ዕድገት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው። ጥራት ያለው የትምህርት ስርዓትን ለማስፈን አለማቀፍ ተሞክሮና ትብብር ያስፈልጋል ተብሏል። በአሜሪካ መንግስት በተዘጋጀውና በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚሁ አውደጥናት ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበራዊ አገልግሎት ዙሪያ ጥራት ያለው ተግባር ለማከናወን ዓለም […]