መጣል የጀመረው ዝናብ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ እንደሚቀጥል ሚትዩሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ
አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የበልግ አብቃይ አካባቢዎች መጣል የጀመረው ዝናብ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ እንደሚቀጥል የብሔራዊ ሚትዩሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚቀጥለው አንድ ወር ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ይኖራቸዋል ብሏል። በኤጄንሲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም እንደተናገሩት በኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ የአርሲና የባሌ ከፍተኛ ቦታዎች እንዲሁም የቦረናና የጉጂ ዞኖች ከመደበኛ […]