loading
ጃፓን የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልትደነግግ ነው::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣ 2013 ጃፓን የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልትደነግግ ነው:: ጃፓን በሶስተኛው ዙር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስረጭት አደጋ ውስጥ መሆኗን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዮሺሂንዴ ሱጋ በመግለጫቸው እንዳሉት አሁን ላይ ሀገሪቱ ያጋጠማትን የበሽታውን ስርጭት ስጋት ለመቀነስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ እንገደዳለን ብለዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ጃፓን ከ4 ቀናት በፊት በ24 ሰዓታት […]

ትራምፕ ነጩን ቤት ከመልቀቃቸው በፊት በቀረቻቸው ሽርፍራፊ ሰዓት አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው::

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ትራምፕ ነጩን ቤት ከመልቀቃቸው በፊት በቀረቻቸው ሽርፍራፊ ሰዓት አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው:: የትራምፕ የቅርብ ሰዎች በተለይ ለስቲቭ ባኖን ይቀርታ እንዳያደርጉ ቢመክሯቸውም በምጫው ያነሱትን ቅሬታ በመደገፋቸው ነው ይቅርታው የተደረገላቸው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡

ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ወታራዊ ልምምዶችን ማድረጓ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ወታራዊ ልምምዶችን ማድረጓ ተሰማ፡፡ የአሜሪካ ቢ 52 ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች በመካከለኛው ምስራቅ መብረራቸውን ተከትሎ ቴህራን በሀገሪቱ ደቡባዊ ጠረፍ አካባቢ ከባድ ልምምዶችን አድርጋለች ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ባለፈው ጃኑዋሪ 3 በጄኔራል ቃሲም ሰይማኒ ላይ ግድያ ከተፈፀመ ወዲህ የአሜሪካ ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች በአካባው ሲበሩ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ ኢራን በሁለት […]

በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ::

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013 በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ:: የሩሲያ የፀጥታ ሃይሎች ከ3 ሺህ በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ማሰራቸው ተሰማ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በቅርቡ ከህመም ያገገሙት የተቃዋሚ መሪው አሌክስ ናቫልኒ ከእስር ይፈቱልን የሚል ጥያቄ ይዘው ነው፡፡

በእንግሊዝ በሙከራ ሂደት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት መልካም ውጤት እያሳየ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣ 2013 በእንግሊዝ በሙከራ ሂደት ላይ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት መልካም ውጤት እያሳየ ነው ተባለ፡፡ የክትባቱ የውጤታማነት ደረጃ ሲለካ 89 ነጥብ 3 በመቶ እንደሆነ የእንግሊዝ የጤና ባለሙያዎች ይፋ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይህን መልካም ዜና እንደሰሙ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡ ኖቫቫክስ የተባለው ይህ ክትባት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመከላከል ውጤታማ ሆኖ የተገኘ […]

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት አዳዲስ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ጥር 24፣ 2013 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት አዳዲስ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸው ተሰማ:: የቀድሞው ፕሬዚዳንት በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ህግ ተላልፈዋል መባላቸውን ተከትሎ ክስ ስለሚጠብቃቸው ራሳቸውን ለመከላkል ነው ይህን ያደረጉት ተብሏል፡፡ ትራምፕ ከሚጠብቃቸው ክስ ይከላከሉልኛል ያሏቸውን ዴቪድ ሾን እና ብሩስ ካስቶር የተባሉ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ትራምፕ አዳዲስ ጠበቆችን ለመቅጠር የተገደዱት የቀድሞዎቹ ጠበቆቻቸው ከሳቸው […]

የአማዞን ቀጣይ ስራ አስፈጻሚ ይሆናል የተባለው ኤንዲ ጄሲ ማነው?

አዲስ አበባ፣ጥር 27፣ 2013 የአማዞን ቀጣይ ስራ አስፈጻሚ ይሆናል የተባለው ኤንዲ ጄሲ ማነው? ከዓለማችን ቁንጮ ቱጃሮች መካከል 2ኛው የሆነው ቤዞስ በግዙፉ የዓለማችን የበይነ መረብ ግብይት ተቋም አማዞን ያለውን ኃላፊነት ለሌላ ሰው እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡ ቤዞስ የአማዞን መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ነው፡፡ ትኩረቱን ወደ ሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች የማዞር ውጥን እንዳለው ያስታወቀው ቤዞስ ዋና ስራ አስፈጻሚነቱን በመጪው […]

በየመን የአልቃይዳ መሪ ካሊድ ባታርፊ በቁጥጥር ስር ውሏል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ጥር 28፣ 2013 በየመን የአልቃይዳ መሪ ካሊድ ባታርፊ በቁጥጥር ስር ውሏል ተባለ:: የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የአልቃይዳ መሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት የክትትል ቡድን ትናንት ሃሙስ ለጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ካሊድ ባታርፊ በቁጥጥር ስር ከዋለ መቆየቱን ጠቁሟል፡፡ በየመን የአልቃይዳ መሪዉ ባታርፊ በፈረንጆቹ 2020 መጀመሪያ አመታ ላይ  ነበር የሽብር ቡድኑን እንዲመራ የተመረጠው እንደ […]

አንግሊዝ የኮሮናቫይረስ የጉዞ ህግ የሚየጥሱ ግለሰቦች ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቀች ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 3፣ 2013 አንግሊዝ የኮሮናቫይረስ የጉዞ ህግ የሚየጥሱ ግለሰቦች ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቀች ፡፡ የእንግሊዝ መንግስት እንዳስታወቀው በተለይ የለይቶ ማቆያ ህግን ተላለፈው የተገኙ ተጓዦች ላይ ትኩረት ያደረገ ህግ ነው የደነገገችው፡፡ እንግሊዝ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ብላ ከዘረዘረቻው ሀገራት ወደ ሀገሯ የሚገቡ ዜጎች ከበሽታው ነፃ መሆናቸው እስኪረጋገጥ በኳራንታይን ውስጥ እንዲቆዩ ያስገድዳል ህጉ፡፡ […]

ዩናይትድ አርብ ኤሚሬት በእስራኤል የሚያገለግላትን አምባሳደር ሰየመች፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 ዩናይትድ አርብ ኤሚሬት በእስራኤል የሚያገለግላትን አምባሳደር ሰየመች፡፡ መሃመድ አል ካጃ በእስራኤል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር ሆነው ተሾመዋል፡፡ መሃመድ አል ካጃ በሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ ጠ/ሚኒስትር እና የዱባይ ገዥ ሼክ መሀመድ ቢን ራ ሺድ ፊት እሁድ ዕለት በአቡ ዳቢ የአል-ዋታን ቤተመንግስት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ሚስተር አል ካጃ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ሕገ- መንግስት እና ሌሎች ህጎች በማክበር ለብሔራዊ ጥቅሟ መከበር ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ቃል […]