
በአዲስ አበባ በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ::
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ ሁለት ድንገተኛ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አያት ጤና ጣቢያ ጀርባ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ በግንባታ ስራ ላይ የነበረ የ35 […]