loading
ለቶማስ ሳንካራ ቤሰቦች የተወሰነው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዩሮ የካሳ ክፍያ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 በፕሬዚዳንት ቶማስ ሳናካራ ግድያ የተጠረጠሩት ፕሬዚዳንት ብላሲ ኮምፓዎሬና አጋሮቻቸው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው፡፡ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓወሬ ከሌሎች 9 ተከሳሾች ጋር ነው ላደረሱት የሞራልና የኢኮኖሚ ጉዳት ካሳውን እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው፡፡ ከኮምፓዎሬ ጋር ፍርድ ከተላለፈባቸው ግለሰቦች መካከል የፕሬዚዳንቱ ጥበቃ ክፍል አዛዥ የነበሩት ሃይሲንቴ ካፋዶ፣ የመከላከያ ኢታማጆር ሹሙ ጊልበርት ዲዬንደሬ ይገኙበታል፡፡


እነዚህ የቀድሞ የኮምፓዎሬ ባለሟሎች ባለፈው ሚያዚያ ወር የእድሜ ይፍታህ ቅጣት የተላለፈባቸው መሆኑን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ፍርደኞቹ ይህን የካሳ ገንዘብ የመክፈል አቅም ሳይኖራቸው ቢቀር መንግስት ለተጎጂ ቤተሰቦች ክፍያውን እንዲፈጽም ይገደዳል ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የሟቹ ፕሬዚዳንት ቶማስ ሳንካራ ንብረት ለቤተሰቦቹ ይመለስ የሚለውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ነው የተሰማው፡፡


እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1983 በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት ቶማስ ሳንካራ በብሄራዊ አብዮት ምክር ቤት ዋና ፅህፈት ቤት ስብሰባ ላይ በተቀመጡበት ከ12 ባልደረቦቻቸው ጋር መገደላቸው የሚታወስ ነው፡፡ የቶማስ ሳንካራ አሟሟት እሳቸውን ተክተዋቸው ወንበሩን በያዙትና ለ27 ዓመታት ሀገሪቱን በመሩት ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓዎሬ የሥልጣን ዘመን ማንም ሰው ደፍሮ የማያነሳው የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ ቆይቷል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *