ማሪዮት ኢንተርናሸናል በኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማስፋፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ተባብሮ መስራት እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡
ማሪዮት ኢንተርናሸናል በኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማስፋፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ተባብሮ መስራት እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ አርን ሶርሰን ከፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘወዴ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡
ኩባንያው አገልግሎቱን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት በያዛቸው እቅዶች ላይ መወያየታቸውንም ከፕሬዚዳንት ጽ/ት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ በተለይም ደግሞ የመስተንግዶው ዘርፍ በፍጥነት እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ብዙ መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ብለዋል፡፡
በዚህ ሂደት ደግሞ ማሪዮት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ በበኩላቸው የኩባንያውን ተነሳሽነትን በማድነቅ የፕሮጀክት ሃሳቦቹ እንዲሳኩ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡