ማይናማር ያሰረቻቸው ጋዜጠኞች የፑሊትዘር ሽልማት አሸነፉ፡፡
ማይናማር ያሰረቻቸው ጋዜጠኞች የፑሊትዘር ሽልማት አሸነፉ፡፡
በማይናማር የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያጋለጡት ሁለት የሮይተርስ ጋዜጠኞች በእስር ቤት እንዳሉ በዓለም ለታዋቂ ጋዜጠኞች የሚሰጠውን ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ጋዜጠኞቹ እንደ አውሮያኑ አቆጣጠር ከ2017 ጀምሮ የተፈረደባቸውን የ7 ዓመት የእስር ጊዜ እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡
የማይናማር መንግስት ጋዜጠኞቹን ያሰራቸው የሀገሪቱን ህግ የሚተላለፍ እና ብሄራዊ ጥቅሟን አደጋ ላይ የሚጥል ዘገባ አሰራጭተዋል በሚል ነው፡፡
የሮይተረስር ዋና አዘጋጂ ስቴፈን አድለር ጀግኖች ጋዜጠኞቻችን በእስር ቤት የሚያሳልፉት ህይዎት አስከፊ ቢሆንም ባሳዩት ከፍተኛ የሞያ ብቃት መሸለማቸው በጣም አስደስቶኛል በሏል፡፡
ዋና ስራ አስኪያጁ ጂም ስሚዝ ደግሞ በሽልማቱ ደስ ቢለንም ጀግኖቻችን ነፃ ሲወጡ ነው ደስታችንን የምናከብረው በማለት ዋ ሎን እና ኪያው ሶዬ ኡ የተባሉት ጋዜጠኞቻችውን ለማስፈታት ትግላቸው እንደማይቆም ተናግረዋል፡፡
ሮይተርስ በሌላ የድርጂቱ አባል በደቡብ አሜሪካ ስደተኞችን ገፅታ በሚያሳይ ፎቶግራፍ ሁለተኛውን ሽልማት ሲያገኝ ሶስት የአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኞችም በሽልማቱ ተካተዋል፡፡
ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ደግሞ በአምደኛው ጀማል ካሾጊ አማካይነት የሽልማቱ ተቋዳሽ ሆኗል፡፡
መንገሻ ዓለሙ