ሞሪታኒያ በሀገሬ ያሉ ስደተኞችን ማስተዳደር አቅቶኛል ስትል የመንግስታቱን ድርጅት ድጋፍ ጠየቀች
ሞሪታኒያ በሀገሬ ያሉ ስደተኞችን ማስተዳደር አቅቶኛል ስትል የመንግስታቱን ድርጅት ድጋፍ ጠየቀች
አርትስ 09/04/11
ሞሪታንያ ውስጥ በሚገኘው እምቤራ የስደተኞች ማእከል በግጭት ምክንያት ከጎረቤት ማሊ የተሰደዱ 57 ሺህ እርዳታ ፈላጊወች ይገኛሉ፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ቲምቡክቱ አካባቢ በፈረንጆቹ 1990 የማሊ ተቃዋሚ ሀይሎች በፈፀሙት ጥቃት እግሬ አውጭኝ ብለው ወደ ሞሪታኒያ የተሰደዱ ማሊያዊያን በከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም የሞሪታኒያ ቅርንጫፍ ሀላፊ ፋዴላ ኖቫክ ስደኞችን በፈቃደኝነት የሚቀበሉ ሀገራት ብዙ ጫና እየደረሰባቸው ነው ብለዋል፡፡
እንደሀላፊዋ ገለፃ ለዚህ ዋነኛው ምክንያቱ ተቋሙ ባለበት የገንዘብ እጥረት ሳቢያ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገንላቸው አለመሆኑ ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም አቀፍፉን ማህበረሰብ ድጋፍ የምንፈልግበት ወቅት አሁን ነው፤ ምክንያቱም በየአካባቢው ግጭት በመበራከቱ የስደተኞች ብዛት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነብን ነው ብሏል፡፡
ስደተኞች በሚኖሩበት እምቤራ ጣቢያ የንፁህ ውሀ፣ የትምህርት እና የጤና አገልግሎት ለመስጠት ቢሞከርም በጥራትም ሆነ በተደራሽነት በቂ እንዳልሆነ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡
የዜጎቿ የቀን ገቢ ከሁለት ዶላር ሚያንሰው ሞሪታኒያ ድንበሯን ለስደተኞች ከፍታ ብተቀበላቸውም ከመንግስታቱ ድርጅት የምታገኘው ድጋፍ እዚህ ግባ የማይባል ነው፡፡