loading
ሰብዓዊ መብት እንዲከበር በምትጥረው ኢትዮጵያ ውስጥ ሰብዓዊ መብት እየተከበረ አይደለም ተባለ

ሰብዓዊ መብት እንዲከበር በምትጥረው ኢትዮጵያ ውስጥ ሰብዓዊ መብት እየተከበረ አይደለም ተባለ

አርትስ 01/04/11

ኢትዮጵያ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች እንዲወጡ ወሳኝ ሚና የተጫወተች ቢሆንም በሃገሪቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈፀማል ተባለ፡፡

ህንን ያለዉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በ70ኛዉ የአለም የሰብአዊ መብት ክብረ በዓል ላይ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዛብሄር በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየታየ ያለዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ከመንግስት ባሻገር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብሏል፡፡

በሌላ በኩል በአለም የሰብአዊ መብት ቀን አከባበር ላይ የተገኙት በምስራቅ አፍሪካ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተጠሪዋ ንዋኔ ቭዌዴ አባሆር በበኩላቸዉ በአለማችን የሰዉ ልጅ ሲወለድ ነፃና ክብርና መብቱ በእኩልነት የተቃኘ ቢሆንም በአፍሪካም ሆነ በመላዉ አለም ሚሊዮኖች የእኩልነት መብታቸዉን አጥተዉ ሲገፉ ይኖራሉ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን በተመለከተም የሰብአዊ መብት አያያዟ ላይ በተሻለ እየሰራች እንደሆነ ይሰማኛል ያሉ ሲሆን፤ አሁንም ግን በሃገሪቱ በህይወት የመኖር መብት ቅድሚያ ሊሰጠዉ ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እንደ አዉሮፓዉያኑ አቆጣጠር በ1948 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲመሰረትና የአለም የሰብአዊ መብት አዋጅ እንዲደነገግ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጓ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *