loading
ሱዳን ወሳኙ የህዳሴው ግድብ ድርድር እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበች::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ20፣ 2012 ሱዳን ወሳኙ የህዳሴው ግድብ ድርድር እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበች::የሱዳን የመስኖና የውኃ ሀብት ሚኒስቴር ቀጣዩ ወሳኝ ድርድር ቁርጥ ያለ ጊዜ ተይዞለት ግልፅ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ አተኩሮ እደካሄድ የሚል ጥሪ አቅርቧል፡፡ሚኒስቴሩ በመግለጫው ድርድሩ የሁሉንም ወገኖች ጥቅም የሚያስጠብቀና ከሚታወቁት አጀንዳዎች ውጭ የሆኑ ሀሳቦች ሳይካተትበት ወደ ውይይቱ መግባተ ያስፈጋል ሲልም አሳስቧል፡፡ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው ካርቱም ባለፈው በአፍሪካ ህብረት የተካሄደው ወይይት ጠቃሚ እና ሚዛኑን የጠበቀ ንእደነበር ገልፃለች፡፡የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ በሶስቱ ሀገራት መካከል ፍትሃዊ እና ህግን መሰረት ያደረገ ድርድር በአፋጣኝ እዲካሄድ ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በቀርቡ በቴክኒካዊ እና ህጋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ድርድር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሀገራቱ ሰሞኑን ባደረጉት ውይይት ልዩነታቸውን አጥብበው ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ ድርድር
ለመቀጠል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *