loading
በሀገሪቱ የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ ሊሰሩ ይገባል ተባለ

በሀገሪቱ የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ ሊሰሩ ይገባል ተባለ

ይህ የተባለው ፓርቲዎች በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በዚህ ውይይት ተፎካካሪ ፓርቲዎች በምርጫ ህግና በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የሚደረጉ ሂደቶች ፣ ደንብና ስርዓቶች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በመድብለ ፓርቲ ላይ የሚሰራው የኒዘርላንድስ  ተቋም በኒዘርላንድ ፓርቲዎች በፖለቲካ ውስጥ ያላቸውን ሚና በተመለከተ በሴናተር ቢን ናፕን አማካይነት አቅርቧል።

ሴናተሩ በሀገራቸው ያለውን የፖለቲካ ባህል ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ያስረዱ ሲሆን፥በሀገሪቱ ያለውን የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳም አብራርተዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ውይይቱ የተከሰቱ ችግሮች ላይ ተወያይቶ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማስቀመጥ የሚያስችል  ነው ብለዋል።

ፓርቲዎች  በጋራ  በመሆን ብሄራዊ አጀንዳ ላይ  ትኩረት  አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባም ተነግሯል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *