loading
በሱዳን አሁንም የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ ተሰግቷል::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2012  በሱዳን አሁንም የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ ተሰግቷል:: በሱዳን የሚዘንበው ከባድ ዝናብ የራይል ወንዝ በ17.5 ሜትር ከፍ እንዲል በማድረጉ ከባድ ጥፋት እያስከተለ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ሱዳን በታሪኳ ከ100 ዓመት ወዲህ እንዲህ የወንዝ ሙላት ገጥሟት አያውቅም፡፡
በዚህም ምክንያት በሱዳን ካለፈው በፈረንጆቹ ኦገስት መጨረሻ 100 ሺህ ቤቶች ሲወድሙ ወደ ከአንድ መቶ ያላነሱ ሰዎች ህይዎታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህ ሳምንት መጨረሻ የአየር ትንበያ መረጃን ተመርኩዞ ባወጣው መግለጫ በመስከረም ወርም ከባድ ዝናብ ስለሚጠበቅ ሁኔታው ተባብሶ እንደሚቀጥል አስጠንቅቋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ ለሶስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገችው ሱዳን የአደጋ ቀጣናዎችን ለይታ ልዩ ትረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች፡፡ የዘንድሮው ክረምት በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጉዳት እያደረሰ የሚገኝ ሲሆን በሴኔጋል እና ካሜሮንም ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ እብደተከሰ ዘገባዎች ያመላክታሉ፡፡ የጎርፍ አደጋው ሰዎች ሳይወዱ ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ስለሚያስገድዳቸው በጊዜያዊ መጠለያ ሲሰባሰቡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እንዳይባባስም ሌላ ስጋት ፈጥሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *